News
ትናንት ማምሸዉ ከባድ ዉጊያ ያስተናገደችዉ ታሪካዊቷ ጎንደር ምሽቱን በልጇቿ ቁጥጥር ስር ገብታ አድራለች።ምሽት 12 ሳአት ላይ የጀመረዉ ዉጊያዉ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዋች ከባድ ትንቅንቅ ተስተናግዷል።
የአማራ ፋኖ በጎንደር በጋሻዉ ክፍለጦር እና የደንቢያዉ አለቃ የደረጃ በላይ የፋኖ አባላት በጋራ በወሰዱት እርምጃ በከተማዋ ሰፍሮ የሚገኛዉን የአገዛዙን ወታደር እንዲሁም የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላትን ሙሉ በሙሉ ከከተመዋ ማስወጣት ችሏል።
የቲወድሮስ ልጆች ምሽቱን ከፍተኛ ድል የተቀናጁ ሲሆን አብዛኛዉን የጠላት ሀይልን መማረክ ችለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከ 80 በላይ የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሳርያ እና 19 የቡዱን መሳርያ መማረክ ችለዋል። 79 የሚሊሻ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ ፋኖን ሲቀላቀሉ 15 የአድማ ብተና አባላት እንዲሁም 33 የአገዛዙ ሰራዉት አባላት በምሽቱ ዉጊያ ፋኖን ተቀላቅለዉ ማደራቸዉ ታውቋል።
ለሶስተኛ ጊዚ ከፍተኛ ዉጊያ የተደረገባት ጎንደር ከተማ የትናንቱ ምሽት ድል የተለየ መሆኑን የጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ ለግዮን ሚዲያ ገልጿል። በምሽቱ ዉጊያ ጎንደርን 90 በመቶ መያዝ የተቻለ ሲሆን በህዝቡ ላይ በደል ሲያደርሱ የነበሩ አካላት ላይም ሙሉ በሙሉ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
በምሽቱ እልህ አሰጨራሽ የጨበጣ ዉጊያ የተደረገ ሲሆን የአገዛዙ ታጣቂ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ የስንቅ አቅርቦቱን ለፋኖ አስረክቦ መዉጣቱ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ከጎንደር ከተማ በቅርብ ዕርቀት ላይ በምትገኛዉ ማክሰኝት ከተማ ተመሳሳይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል። በከተመዋ የደፈጣ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን በተፈፀመዉ የደፈጣ ጥቃት አንድም የጠላት ሀይል አለመትረፉን የጎንደሬ በጋሻዉ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ባሻ ስጦታዉ ለግዮን ሚዲያ ተናግሯል።
ላለፉት ስምንት ወራት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ያለዉ የጉና ክፍለጦር ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርግ መቆየቱንም የጉና ክፍለጦር ም/ አዛዥ ሻምበል አምሳሉ ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
በጉና በጌምድር ጉና ተራራ ላይ ሲደረግ የቆየው የአራት ቀኑ ትንቅንቅ በፋኖ ድል የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህ አዉደዉጊያ የ 92ኛ ክፍለ ጦር የዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል ብርሀኑ የተባለ አመራር እስከነ አጃቢዎቹ ድል ሲደረግ ሁለት መስመራዊ መኮነኖችም ቆስለዉ ሆስፒታል መግባታቸዉን የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ በነበረዉ አዉደዉጊያ መትረፍ የቻሉ 47 የብርሀኑ ጁላ ወታደሮች እጅ የሰጡ ሲሆን ከ አንድሻለቃ በላይ ሀይሉም በጉና ተራራ ስር ተደምስሷል።
በሌላ መረጃ የጉና ክፍለጦር በእስቴ ልጫ ግንዳጠመም እና ለወየ በደረጉት ዉጊያ የጠላትን ሀይል አከርካሪዉን በመምታት የዞት የነበረዉን ቦታ ማስለቀቅ ችለዋል። በአሁኑ ሰአት የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ቀጠናዉን ተቆጣጥሯል።
ከክልሉ መዲና ባህርዳር አስቴ የሚወስደዉ አዉራ ጎዳና ሙሉ በሙሉ የተዘጋ ሲሆን ከደብረታቦር እስቴ የሚወሰደዉ ሌላኛዉ አዉራ ጎዳናም ዝግ መደረጉም ተገልጿል። በደራ ሀሙሲት አንበሳሜ ከተማ ተደብቆ የሚገኛዉ የጠላት አብይ አህመድ አሊ ወታደር የገላወዲወስ ልጆችን ክንድ መቋቋም ስላልቻለ ከተመዋን ለቆ ወቷል።
በዚሁ አካባቢ ዛሬ መጋቢት 23/2016/ዓ/ም ከባድ ዉጊያ ሲደረግ የዋለ ሲሆን በአንበሳሜ ከተማ የሰፈረዉ ፀረ አማራዉ የብልፅግና ፓርቲ ወታደር ከተማዋን ለቆ ወቷል። ይህ ፀረ አማራዉ ሀይል ከተማዋን ለቆ ሲወጣ ከ5 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን መግደሉ የአካባቢዉ ኗሪዋች ገልፀዋል። አሁንም በደራ ሀሙሲት እና በእስቴ አልፎ አልፎ የተኩስ ልዉዉጥ አየተደረገ መሆኑን የአማራ ፋኖ በጎንደር የጉና ክፍለጦር የጣና ገላው ዲወስ ዋና አዛዥ ሻለቃ አዲሴ ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
##########################
##########################
በጎጃም ደምበጫ ከተማ ጨረቃ ወረዳ አካባቢ በተደረገ ጥቃት የአማራ ፋኖ ድልን ተቀዳጀ። ፋኖ በጠላት ሃይል ላይ በወሰደው እርምጃ የአገዛዙ ጦር ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። በተያያዘ ዜና በቤተ አማራ አምባሰል ወረዳ ግሸን ደብረ ከርቤ ልዩ ቦታው ሃሙሲት በሚባል ስፍራ የብልጽግና ሰራዊት በፋኖ ላይ ጥቃት ቢከፍትም የአገዛዙ ሰራዊት ተደምስሷል።
በሌላ በኩል በወለጋ በንጹሃን አማራ ገበሬዎች፣ እናቶች እና ህፃናት ላይ የብልፅግናው ኦነግ ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል።
###################
####################
ከባለፈው ትምህርት መውሰድ ያቃታት ህወሃት የአማራን ህዝብ ለማጥቃት እየሰራች ትገኛለች። መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም ህወሃት ጦሯን ወደ ወልቃይት እና ራያ እንዳስጠጋች ነው። ባለፉት ቀናቶች ህወሃት የራያ አላማጣ ቀበሌዎችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት በመክፈት የአማራ ህዝብ ላይ ጉዳት ማድረሷ ይታወሳል።
በሌላ ዜና “የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም” በሚል መሪ ቃል የወፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢ ነዋሪዎች ሰልፍ አድርገዋል።
######################
######################
አብይ አህመድ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመወያየት ያቀረበውን ጥያቄ የተወሰኑ የሃገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲ ተውካዮች ውድቅ አደረጉት።
አብይ አህመድ ፈቃደኛ ከሆኑ ከተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ዛሬ ውይይት ጀምሯል። በዚህ መድረክ ከተጋበዙት መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)ና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር(ONLF)ን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደማይገኙ ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።
እንደ ሬዲዮ ዘገባው ዘጠኝ አባላት ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በውይይቱ አይሳተፍም። በብሔር ከተደራጁት የክልል እና ሃገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ጥሪ ያቀረበው የብልጽግና አገዛዝ የሚፈልገውን ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል።
ስድስት ስድስት አመራሮች ከሃገር አቀፍ ፥ እንዲሁም ሶስት ሶስት ተወካዮች ከክልል ፓርቲዎች ስብሰባውን እንዲሳተፉ ነበር አገዛዙ ጥሪ ያደረገው። ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቱ የማያባራ ጦርነት በማካሄድ የሚታወቀው የብልጽግናው አገዛዝ የሃገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ ማስከበር ባለመቻሉ ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል።
የአገዛዙ ወታደሮች በተለይም በአማራ ክልል እየፈጸሙ ባሉት ወረራ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈጸማቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እየደረሰባቸው ይገኛል።
######################
######################
የአማራ ብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች ስበሰባ በሁለት ጎራ ተከፍሎ ያለስምምነት መጠናቀቁ ተገልጿል። የአማራን ህዘብ ላለፉት አምስት አመታት ከጠላት ጋር አባሪ በመሆን ዋጋ ሲያስከፍል የቆየዉ የክልሉ ብልፅግና ሰሞኑን ስብሰባ ተቀምጦ ያለ ስምምነት መበተኑ ታዉቋል።
ስብሰባዉ ህዝቡን በፈለግነዉ መንገድ ማስተዳደር አልቻልም በመሆኑም ከብልፅግና አፈንግጦ የወጣዉን ህዝብ በወታደራዊ ሀይል በመዳፋችን ውስጥ ማስገባት አለብን በሚል መሪ ቃል ሲሆን የክልሉ ብልፅግና መሪ ቃሉን ቀይሮ ለሚዲያ ሽፍን ማቅረቡ ድርጅቱ የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን በተግባር ያየንበት ነዉ ሲል በስብሰባዉ ተካፋይ የሆነ ከፍተኛ የብልፅግና አመራር ለግዮን ሚዲያ ተናግሯል።
ስብሰባዉ በሁለት ጎራ የተከፈለ ሲሆን ሁለቱም ከተለጠፉት የኦህዴድ አለቆች ዝና እና ሹመት እንዲሁም ጥቅም ለማግኛት የአማራን ህዝብ እኔ ላስገድለዉ በሚል የስልጣን ሹኩቻ ለማግኘት ያደረጉት እሰጣገባ ነዉ።እሰጣ ገባዉ ቦክስ ቀረሽ ንትርክ ሲሆን ያለስምምነት ተለያይተዋል።
በሰሞኑ የህወሃት ትንኮሳ ግራ የተጋቡት የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ባንዳዋች በስብሰባው ከመንግስት ጎን እንቁም ወይስ ከህዝቡ ጎን በሚል ሌላኛዉ ክርከር ያለስምምነት የተቋጨ ሲሆን ህወሃትን በሚዲያ በማዉገዝ የተመለሱ የአማራን እርስቶች ማስመለስ አይቻልም መንግስትም እነዚህን ግዛቶች ለህዋት አሳልፎ እንደሚሰጥ ጥርጥር የለንም ያሉት ደግሞ ከሁለቱ ጎራ ውጭ ሆነዉ ሀሳባቸዉን የቀረቡት የቀለመወርቅ ቲም በመባል የሚታወቁት የብልፅግና ተወካዮች ናቸዉ። እነዚህ የብልፅግና ሰዎች ከልባቸዉ ይሁን ባይታወቅም በስብሰባዉ ላይ ባነሡት ጠንካራ ሀሳብ መረበሻቸዉንናማስደንገጣቸዉን የውስጥ ምንጫችን ገልጿልናል።
የአማራ ህዝብን ከኦህዴድ ሰዋች ተለጥፈን የነሱን ስልጣን ለመጠበቅ ብለን ለክፉ አደጋ ጥለነዋል ያሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ይህንን የተከበረን ህዝብ ለማዋረድ የነሱን አጀንዳ በማስፈፀም በሚዲያችን ደግሞ ህዝባችንን መግለጫ በማዉጣት እሸጎድነዉ ነዉ ሲሉ ጠንካራ ሀሳብ አንስተዋል።
የአማራን ግዛቶች አሳልፈን ላለመስጠት ከማን ጋ እነሰለፍ ያሉት የአማራ ብልፅግና ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።እነዚህ ሰዎች በህዝብ ዘንድ ታሪክ የማይዘነጋዉ ስህተት ለመስራት ግብግብ የገጠሙ ሲሆን መጨረሻቸዉ ወርደት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ሲል ምንጫችን ገልጿል።
በስብሰባዉ ህዝቡን በመካዳችን ህዝቡን ብንጠጋዉ አያምነንም ስለሆነም እስከመጨረሻዉ ከፌደራሉ መንግስት ጎን በመሆን ሁኔታዉን መከታተል አለብን ያሉት የብልፅግና አመራሮቹ በአንፃሩ በትንሽ ሰዋች ደግሞ ጠንከር ያለ እና እዉነተኛ ደፋር ሀሳብ ተሰንዝሯል።
ሀሳቡን የሰነዘሩት በነቀለመወርቅ ቲም ውስጥ የሚገኙ ነብልፅግና አባላት ሲሆኑ አማራዉ ታሪካዋ ክብሩን ለማስጠበቅና የተቃጣበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንዲሁም ታሪካዊ ግዛቶቹን አስከብሮ ለትዉልድ ለማቀባበል ከዚህ ቦታ ያለነዉ የክልሉ የመንግስት አባላት ከጀግናዉ የአማራ ፋኖ ጎን መሰለፋ አለብን ሲሉ የአማራ ህዝብ የሚድንበትን ዋናኛ አማራጭ በግልፅ አሰረድተዋል።
በሌላ መልኩ ከህዝቡ ሙሉ በሙሉ የነጠለን የእናንተ አይነቱ አስተሳሰብ ያለዉ ፅንፈኛ ሀይል ነዉ በማለት ዛቻና ማስፈራሪያም በቡድኑ በኩል የተሰጣቸዉ መሆኑ ተገልጿል። ስብሰባዉ ሶስት ቀናት ያፈጀ ሲሆን ያለስምምነት እንደተቋጨ እና በባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በመሰጠት ተጠናቋል ያለዉ የአሚኮ ዘገባ ሀሰት መሆኑን ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የብልፅግና አባል ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
######################
######################
የአማራን ህዝብ እንደ ጠላት እንዲፈረጅ ኢላማ አድርጎ እየሰራ ያለው የብልጽግና አገዛዝ ሰሞኑን በ52 ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተ አስታውቋል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች የተለያየ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የህዝብ መብት ተሟጋቾች እንደሆኑ ነው በክሱ ላይ የሰፈረው የስም ዝርዝር የሚያሳየው፡፡
የክሱ ይዘት አሁንም አገዛዙ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ የሚያሳይ እንደሆነ የክሱ ጭብጥ ያስረዳል፡፡
በእነዚህ 52 ግለሰቦች ላይ ክስ የተመሰረተው “ አገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እሳቤ ብቻ አልተደራጀችም “ ስለዚህ “ በአማራ አስተሳሰብ ብቻ መገዛት አለባት“ በሚል የሀስት ውንጀላ እንደሆነ ተገልጾል፡፡
የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለው ግፍና በደል መፍትሄ እንደሚሻ ላለፉት 5 አመታት በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል:: ነገር ግን በአማራ ጥላቻ የሰከረው የብልጽግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ ማፈናቀልና መግደል አልበቃ ብሎት በህዝብ ላይ ጦርነት ካወጀ ድፍን 8 ወራት ተቆጥረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት አገዛዙ በፋኖ እየደረሰበት ያለውን ሽንፈትና ውርደት አምኖ መቀበል ሲያቅተው በፈጠራ ክስ ፖለቲከኞችን ፣ ጋዜጠኞችን እና የአማራ ተወላጆችን እያሳደደ በማሰር ላይ እነደሚገኝ የተለያዩ የዜና ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
የአብይ አህመድ አገዛዝ የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ነው በእስክንድር ነጋ፣በዘመነ ካሴ እና በሌሎች 52 ተጨማሪ ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረትኩ የሚለው:: የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩትን አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና የአብን የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለም በክሱ እንደተካተቱ ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው አስፍሪል.።
#####⨳################
######################
በመጨረሻም
የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሚዲያ ሽፋን ተበልጠናል የሚል የትእዛዝ ደብዳቤ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላኩ።
ጀነራሉ በላኩት ደብዳቤ ላይ በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ የመከላከያ ሰራዊቱ የህይወት መስዋእት እየከፈለ ለወራት መዝለቁን በመጥቀስ በመንግስት ሚዲያው ዘርፍ የተሰራው ስራ ከጠላት ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን በግምገማ ለይተናል ይላል።
ግምገማውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት መደረጉንም ደብዳቤው ይገልጻል። ካሉት የሚዲያ ብዛት እዚህ ግባ የማይባል ስራ ነው የተሰራው የሚለው የምክትል ኢታማዦሩ ደብዳቤ ከዚህ በኋላ ተቋሙ ወደ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሚልካቸውን ዜናዎች ጨምሮ የሰራዊቱን ክብርና ዝና ከፍ የሚያደርግ ዘገባ እና ፕሮግራም ያለማቋረጥ እንዲሰራ ሲል ያሳስባል። በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሰራዊቱ የህዝብ ድጋፍ እንዳላገኘም ደብዳቤው ጠቅሷል።