የዕለቱ ዜናዎች
አገዛዙ በአዲስ አበባ በህቡዕ ሲሰራጩ በነበሩ መልእክቶች መሸበሩ ተሰማ። ድርጊቱን የፈፀመው አማን የተባለው ቡድን ሳይሆን አልቀረም ተብሏል።
አገዛዙ ወደስልጣን የመጣበት መጋቢት 24 ቀን በትሩን ካሳረፈባቸው አካባቢዎች ውስጥ አዲስ አበባ አንዱ ነው። የብልጽግና ቁንጮ ወደ ስልጣን እንደመጡ በአዲስ አበባ ጉዳይ ወደ ኋላ እንደማይሉ ለማስጠንቀቅ ግዜ አልወሰደባቸውም።
ከቤት መፈናቀል ከስራ መባረር የጅምላ እስር የኑሮ እንግልት የአዲስ አበባ እጣ ፋንታ ከሆነ ውሎ አድሯል። ይህንንም ተከትሎ አገዛዙን ለመጣል አማን የተባለው የህቡእ አደረጃጀት ተመስርቷል ቡድኑ ትላንትና ለሊት ጎተራና ቦሌ ባሉ አካባቢዎች መጋቢት 24 ጥቁር ቀን በማለት በርካታ ባነሮችን ሰቅሏል።
በሁኔታው የተደናገጠው አገዛዙ በወታደሮች በመታገዝ መልእክቱን ሲያስነሳ ታይቷል ይህም ቢሆን ግን መልእክቱ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጆሮ ከመድረስ ያገደው ነገር የለም።
በአሁኑ ወቅትም የከተማዋ ድባብ መጋቢት 24 ጥቁር ቀን መሆኑን በሚያሳብቅ ሁኔታ እያለፈ ነው። በተጨማሪም በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የዛሬዋ ቀን ጥቁር ቀን በሚል ታስቦ እንደዋለ ከሪፖርተሮቻቸን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
=========================////////////////=============================
የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር በአማራ ክልል ዳግም የድሮን ጥቃት ጀመሩ። ሁኔታው ዳግም ውጥረትን አንግሷል።
የአገዛዙ ድሮኖች በሰሜን ጎንደር አካባቢ የድሮን ጥቃት መፈፀማቸው የግዮን ምንጮች አረጋግጠዋል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቁጣ ምክንያት ጋብ ብሎ የነበረው የድሮን ጥቃት ማገርሸቱ አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል ከወራት በፊት በሰሜን ሸዋ ህፃናት ሳይቀሩ በድሮን ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም ይህን ተከትሎም የባይደን አስተዳደር በአገዛዙ ላይ ቁጣ ሰንዝሯል።
በዚህም ሳያበቃ ገንዘብ እስከመከልከል የሚደርስ እርምጃም በመውሰድ ላይ ነው በዚህ የተደናገጠው አገዛዙ ለሳምንታት ዝምታን ቢመርጥም አሁን ግን አገርሽቶበታል
በሰሜን ጎንደር የተፈፀመው ጥቃት ያደረሰው ጉዳት በቁጥር ባይታወቅም ጦርነት ግን በአካባቢው እንዳልነበረ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን ለአራት ኪሎ ቅርብ የሆኑ ግለሰብን አነጋግረን ነበር
ግለሰቡ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከፍተኛ የመረበሽ ስሜት ይታይባቸዋል በተለይ በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ እያስጨነቃቸው እንደሚገኝም ይገልፃሉ ከዛም አለፍ ሲል በአካባቢው የድሮን ጥቃት ሲፈፀም ከፍተኛ የመረጋጋት እና የደስታ ስሜት እንደሚታይባቸውም አልሸሸጉም በአጠቃላይ ስናየው ሰውየው አለም አቀፉን ማህበረሰብ ፈርተው እንጂ 24 ሰአት ድሮን ቢያዘንቡ ደስተኛ እንደሚሆኑ ግምታቸውን አስቀምጠዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በሰሜን ጎንደር የፈፀሙት የድሮን ጥቃት ላለቀባቸው ሰራዊታቸው የበቀል እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ወይም የውስጥ አዋቂው ግለሰብ እንዳሉት የግል እልሀቸውንም ለመወጣት ሊሆን ይችላል ሲል ሪፖርተራችን ዘግቧል።
=======================///////////////////////================================
ሰሞኑን በጭንቀት ላይ የሚገኙት የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት ላይ ናቸው። በውይይቱ የተሳተፉ አካላት ዋናውን የሀገሪቱን ችግር የማይወክሉ ቢሆንም ለድምቀት ያህል ግን አዳራሹን ሲሞሉት ታይተዋል። ይህም ቢሆን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈታኝ ጥያቄዎች ማምለጥ አልቻሉም።
ዛሬ ከተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ጋር በነበረው ቆይታ ተቃዋሚ ነን የሚሉት ኢዜማና አብን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙገሳ ቢያቀርቡም ሌሎች ተቃዋሚዎች ግን ከባድ ጥያቄ ሰንዝረዋል። ከጥያቄዎቹ ውስጥም ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ይታሰራሉ ስልጣን ላይ ሲመጡ የማስረው ዜጋ የለም በማለት ቃል ገብተው ነበር የሚል ይገኝበታል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በሰጡት ምላሽ የግብፅ ተላላኪዎች መሆናችሁን ስለማላውቅ ነበር ቃል ገብቼ የነበረው በማለት ጠያቂዎቹን ወርፈዋል።
እርስዎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይስ እንዳሉት ንጉስ ነዎት ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄም እኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ በማለት ከዚህ በፊት በአደባባይ የተናገሩትን ሀሳብ መቀየራቸውን ገልጸዋል። የሀገሪቱን ሀብት እንዳስፈላጊነቱ ወደ ጦርነት አውለዋለሁ ብለዋል ይህስ ተገቢ ነው ወይ ብለው ያምናሉ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸውም የመበሳጨትና የንዴት ስሜት ይታይባቸው እንደነበር ስብሰባው ውስጥ የነበሩ አንድ ታዛቢ ገልፀዋል።
ለጥያቄው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መልስ እንደዚህ አይነት ሀሳብ አንስተው እንደማያውቁ ክደዋል ።
በዚህም ምክንያት ለሙገሳ ረሀባቸው የጠሩት ስብሰባ ማምሻው ላይ ያለ ውጤት ተበትኗል በስብሰባው መሀል ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የስሜት መረበሽና አልፎ አልፎም ስድብ የተቀላቀለበት መልስ ሲሰጡ ታይተዋል።
የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ስብሰባውን በተመለከተ አጭር ዘገባ ከማቅረብ ውጭ ወደ ዝርዝር ሀሳብ ከመግባት ተቆጥበዋል በሚቀጥሉት ቀናት ሙሉ ውይይቱን ካቀረቡም ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች ቆርጠው እንደሚያወጡት ይጠበቃል።
ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት የእንወያይ ጥያቄ በዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውድቅ እንደተደረገባቸውም አይዘነጋም።
============================////////////////////////========================
አብይ አህመድ የአማራን ህዝብ ለማስጨፍጨፍ ፈርሞ የላከው የጦር ጀት በረቡ ገበያ እና በቢቡኝ ወረዳ ጮቄ በሚባል ተራራማ አካባቢ ተልዕኮውን ሳያሳካ ተከሰከሰ።
በጎጃም በስናን እሮብ ገበያ እና በቢቡኝ ወረዳ በጮቄ ተራራማ አካባቢ ላይ የተሰጠውን ተልዕኮ ሳይፈፅም ከምድር ጋር ተላትሟል። ይህ ክስተት ሲፈፀም አማራ ክልል ውስጥ አሁን ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
ሃገር በጨፍጫፊዎች እጅ ላይ ወድቃ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም በማይገቡበት፣ በቀን አንዴ እንኳን ለመመገብ ችግር በሆነበት በዚህ ወቅት የዘር ጭፍጨፋ የተለመደ ተግባር ሆኗል ።
አገዛዙ ቢሊዮን ዶላር አውጥቶ የጦር ጀትና ቦንብ እያስገባ ንፁሃንን ለመጨፍጨፊያ ሲያውል እያየ ዝም የሚለው ቢበዛም የአማራ ህዝብ ግን አይደለም ወታደሩ ይቅርና የአማራ ተራሮችና ሸለቆዎች የወራሪውን ሰራዊት መውጫ አሳጥተውታል ።
በሰሜን ሜጫ ብራቃት በፋኖዎች አስደናቂ ጀብድ ተሰራ። በሰሜን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ልዩ ስሟ አጣሪ በተባለች ቦታ ከ50 በላይ የብልጽግና ሰራዊት ፋኖ ባጠመደው ፈንጂ ተደምሰዋል ።
ከአንድ ወር በፊት በዚሁ ቦታ የገባው የብልፅግና ሰራዊት የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ከአርባ በላይ ንፁኃንን ረሽኗል። በዚህም ምክንያት የተበሳጨው የአካባቢው ማህበረሰብ አንቅሮ የተተፋው የብልግና ሰራዊት ከብራቃት አስወጥቶት ነበር።
ከገርጨጭ የተባረረው የብልግና ሰራዊት እንደገና ወደ ብራቃት ሲንቀሳቀስ የአማራ ፋኖ በጎጃም ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አበራ ሙጬ ሻለቃ ፋኖ ልዩ ኦፕሬሽን ሰርቷል ።
የታደሰ ሙሉነህ ልጆች በአሁኑ ሰዓት እንደተለመደው ብራቃት ከተማን በእጃቸው አስገብተዋል።።
በጎጃም ማንኩሳ ውሀ በመዝጋት ጭምር ህዝብን ሲያሰቃዮ የቆዮት ማንኩሳ ወረዳ የብልግና አመራሮች ላይ በፋኖ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በጎጃም ማንኩሳ ላይ በተደረገ ጥቃት የማንኩሳ ወረዳ ኃላፊ እና ምክትል አስተዳዳሪን ጨምሮ 4 የብአዴን አመራሮች በፋኖዎች ህዝብ ለፍርድ አቅርቧቸዋል ::
ውሀ በመዝጋት ጭምር ህዝብ ሲያሰቃዮ የቆዮት የብአዴን አመራሮች በማንኩሳ ሻለቃ አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ሲሉ የችግሩ ሰለባዎች አስረድተዋል ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም በሁሉም አካባቢዎች ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ ። ከእነዚህም የሳሙኤል አወቀ ብርጌድ ከዛሬ ጠዋት 12:00 ጀምሮ ከጠላት ጋር ተናንቋል ።
ብርጌዱ ጎጃም ደብረወርቅ ላይ ልዩ ቦታው ፈለገ ጭየ አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጋድሎ ማድረጉ ታውቋል ። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ብርጌድ የፋኖ አደረጃጀቶች ሽፋን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል ።
በተያያዘ መረጃ ግንደወየይን የነበረው መከላከያ ወደ ደብረወርቅ ፈለገ ጨየ ሂዷል።ግንደወይን ምንም የብልግና መከላከያ የለም በዚህ ሰዓት ከተማ ውስጥ ያለው ፓሊስ ብቻ መሆኑ ታውቋል ።
አገዛዙ በሞጣ፣ ፍኖተሰላም፣ ደብረማርቆስና ቢቸና ከተሞች የኃይል መሳሳት ስላለ አዲስ ኃይል እንዲገባ ትዕዛዝ ሰጠ ።ይህን ትዕዛዝ ለመፈፀምም እንቅስቃሴ መኖሩን ለመረዳት ተችሏል።
በተጨማሪም ጎጃም ውስጥ “ከከዚህ በፊቱ በተለየ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፋኖ እየሰለጠነ ነው” በሚል አገዛዙ የመረጃ ሰዎችን ከአዲስ አበባ ሞጣ በህዝብ አውቶቡስ ከትላንት ጀምሮ እያስገባ እንደሆነ ታውቋል።
የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ተልዕኮም በቀጠናው ያለውን የፋኖ የስልጠና እንቅስቃሴ መረዳትና የፋኖን አሃዛዊ መረጃ መሰብሰብና አለፍ ሲልም እንደ አስተኳሽ ስምሪት መውሰድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም አቤ ጉበኛ ብርጌድ ታላቅ ጀብድ ሰርቷል። የአማራ ፋኖ በጎጃም አቤ ጉበኛ ብርጌድ በአንድ ኦራል ሙሉ ሲግተለተል የነበረን የአገዛዙ ወታደሮች በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የአገዛዙን አንድ የኦፐሬተር ኃላፊና ከ10 በላይ ጨፍጫፊ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ።
መታፈሪያ ሃይሌ ከጎጃም
====================/////////////////////===================================
በሰሜን እና በደቡብ ወሎ ዞን ድንበር አካባቢ በ014 ቀበሌ ወፋጮ ልዩ ስሙ ቀዝቃዚት በምትባል ቦታ 57 የአገዛዙ ኃይል ተደመሰሱ።
አካባቢው በወቅቱ በጉም ተሸፍኖ ነበር። ወደ አካባቢው የገባው ኃይል በጉዞ ላይ እያለ በጉም በተሸፈነው አካቢቢ ሳይተያዩ ሁለቱም ተፋላሚዎች ፊት ለፊት ተገናኙ።
በቅርብ ርቀት የተገናኙት ፋኖዎች እና የሚሊሻ፣ የአድማ ብተና እና የመከላከያ አባላት በሳንጃ ሳይቀር በጨበጣ እልህ አስጨራሽ ውጊያ 57 የአገዛዙ ኃይል አባላት መሞታቸውን ሪፖርተራቸን ቸርነት ተሰማ ከሰሜን ወሎ እዜት በር አድርሶናል።
ቸርነት ተሰማ ከወሎ
======================////////////////===================================
በደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ እየሱስ ትናንት ማምሸዉን ጀምሮ እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ እየተደረገ ይገኛል።
በወረዳዉ የተለያዩ አካባቢዋች ከባድ ዉጊያ ሲደረግ ያመሸ ሲሆን ከምሽቱ አንድ ሳአት እስከ ምሽቱ ስድስት ሳአት ድረስ በመካነ እየሱስ ከተማ ከባድ ትንቅንቅ ሲደረግ አምሽቷል።
የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ የፋኖ አባላት በምሽቱ በነበረዉ ግብግብ የጠላት አብይ አህመድ ጦር በመሸገበት ምሽግ መቅረት ችሏል።
ፀረ አማራዉ የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ወታደር በከተመዋ ኗሪዋች ላይ አሰቃቂ ግፍ መፈፀሙን ተከትሎ የአማራ ህዝብ የክፉ ቀን ደራሽ የሆኑት የእስቴ ዴንሳ የፋኖ አባላት ፈጥነዉ ከተማ በመግባት ወገኖቻቸዉን ከሞት መታደግ ችለዋል።በከተመዋ ኗሪዋች ላይ የዘረፋ ተግባር እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን በግፍ ሲገድል የቆየዉን የጠላት ሀይልን አፀፋዊ እርምጃ ወስደዉበታል።
ብዛት ያለዉ የሚሊሻ አባላት እንዲሁም የአድማ ብተና አባላት ሲደመሰስ የቀረዉ ደግሞ ምርኮኛ ሆኗል።እነዚህን ፀረ አማራ ሀይሎች በመያዝ የከተማዋን ኗሪዋች ግብር ክፈሉ በማለት ግፍ ሲፈፅሙ የነበሩ የብልፅግና አጎብዳጅ ባንዳዋች እርምጃ ሲወሰድባቸዉ ቀሪዋቹ ደግሞ ተይዘዉ ተወስደዋል።
ከተማዋ በአሁኑ ሳአት በሁለቱ ሀይሎች እጅ ውስጥ ስትገኝ ዙሪያውን በጀግኖቹ የእስቴ ዴንሳ ልጆቾ ታጥራ ተገኛለች።በጀግኖቹ መዳፍ ስር የሚገኛዉ የብርሀኑ ጁላ ፀንፈኛ ሀይል የስንቅ አቅርቦት ስለተቋረጠበት በርሀብ እየተቀጣ መሆኑ ተገልጿል።
ከዞኑ መናገሻ መነሻዉን ያደረገዉ የብርሀኑ ጁላ ፀረ አማራዉ ሀይል እስቴ ላይ ለታፈነዉ ሰራዉት ስንቅ ይዞ በሚጓዝበት ወቅት ከመካነ እየሱስ ከተማ በአስር ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኛዉ ለወየ ከተማ በቦንብ የደፈጣ ጥቅት ተፈፅሞበታል።
በጥቃቱ የጠላትን ሀይል ስንቅ የጫነዉ ኦራል ተሽከርካሪ እና ከ20 በላይ ሰራዉት ሙሉ በሙሉ ኪሳራ ደርሶበታል።
በተያያዘ ዚና በፋርጣ ወረዳ ጋሳይ ከተማ ሰፍሮ የነበረዉ ሀይል ቁስለኛ ለማዉጣት ወደ ለዋየ በሚጓዝበት ወቅት ጎማራ ወንዝ ላይ የደፈጣ ጥቃት ተሰንዝሮበት ወደ መጣበት ተመልሷል።
በእነ ሻለቃ ቆራጡ አንዳርጌ እና ሻለቃ ብርቃየዉ ደምሴ የሚመራዉ የዴንሳ ፋኖ የመካነ እየሱስ ከተማን ሁለት ቀበሌ በዕጃቸዉ ማስገባት ችለዋል።
በከተማዋ የሚገኛ 20 በላይ ባለሀብቶች ለመከላከያ ቀለብ የሚሆን 10 ሚሊዮን ብር እንዲሰጡ ግዳጅ የተጣለባቸዉ ሲሆን ገንዘቡን አንሰጥም በማለታቸዉ የአገዛዙ ሰራዉት አፍኖ ከወሰደ በኋላ እስካሁን ድረስ የት እንዳደረሳቸዉ አለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ለግዮን ሚዲያ ገልፀዋል።
በነበረዉ እልህ አስጨራሽ ዉጊያ የፍኖን ክንድ መቋቋም የተሳነዉ የአገዛዙ ሰራወት ሁለት ሰላማዊ ዜጎችን በግፍ ከገደለ በኋላ ከከተማዋ ወጣ ብሉ በሚገኛዉ ማቢ አቦ ተራራ ሰፍሮ ይገኛል።በዚሁ ተራራ ስራ የሚገኙ ኗሪዋች ሀብት እና ንብረት በመዝረፍ ኗሪዋቹን ከቀለሱት ቅያቸዉ እንዳፈናቀላቸዉ ኗሪዋቹ ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በከተመዋ ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው የአገዛዙ ወታደር ተስፋ በመቁረጥ አሰቃቂ ግፎችን በህዝብ ላይ እፈፀመ ይገኛል።
በተጨማሪም ሰሞኑን ከእስካሁኑ በተለየ ጠንካራ ትግል እያደረገ የሚገኛዉ የጎንደር ፋኖ ታላቅ ድል መቀናጀቱ ተገልጿል።
በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ እና በለሳ እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዳባት፣አጅሬ እና ጃናሞራ እንዲሁም በምዕራብ ጎንደር አርማጭሆ እየተደረገ ባለዉ የህልውና ትግል ፋኖ ከፈተኛ የተባለለትን ድል ማስመዝገቡን የጀግናው ጎቤ መልኬ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ሻለቃ ሲሳይ አሸብር ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
የጎቤን ምድር የሚረግጥ የጠላት ሀይል የአርማጭሆ የአፈር ሲሳይ ይሆናል ያለዉ ባለቁንዳለዉ የጦር አለቃ ሰሞኑን በነበረዉ የጦር ሜዳ ዉሎ ብቻ ከ 3 መቶ በላይ የጠላት ሀይል መደምሰሱን ገልጿል።
በዚህ ዉጊያ ከ17 በላይ የቡድን መሣርያ መማረካቸውን ገልጿል። አርማጭሆን እሚደፍር የጠላት ሀይል ካለ መጨረሻዉ ሞት ነዉ ያለዉ ሻለቃ ሲሳይ አሸብር በአሁኑ ሳአት ቀጠናዉን 95 በመቶ ፋኖ እያስተዳደረዉ መሆኑን ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
ቶማስ ፍትህ ከጎንደር
======================/////////////////////////===============================
በመጨረሻም
የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሚዲያ ሽፋን ተበልጠናል የሚል የትእዛዝ ደብዳቤ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላኩ።
ጀነራሉ በላኩት ደብዳቤ ላይ በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ የመከላከያ ሰራዊቱ የህይወት መስዋእት እየከፈለ ለወራት መዝለቁን በመጥቀስ በመንግስት ሚዲያው ዘርፍ የተሰራው ስራ ከጠላት ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን በግምገማ ለይተናል ይላል።
ግምገማውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት መደረጉንም ደብዳቤው ይገልጻል።
ካሉት የሚዲያ ብዛት እዚህ ግባ የማይባል ስራ ነው የተሰራው የሚለው የምክትል ኢታማዦሩ ደብዳቤ ከዚህ በኋላ ተቋሙ ወደ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሚልካቸውን ዜናዎች ጨምሮ የሰራዊቱን ክብርና ዝና ከፍ የሚያደርግ ዘገባ እና ፕሮግራም ያለማቋረጥ እንዲሰራ ሲል ያሳስባል።
በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሰራዊቱ የህዝብ ድጋፍ እንዳላገኘም ደብዳቤው ጠቅሷል።
===============================////////////////==========================