የዕለቱ ዜናዎች
የአገዛዙ ጦር አዛዦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ
ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአለም አቀፍ ሰላም አስከባሪነት እንዲታገዱ ጠይቋል።
በአማራ ክልል አገዛዙ የፈፀመው ጭፍጨፋ አሁንም አለም አቀፍ መነጋገሪያ መሆኑን ቀጥሏል።
የአገዛዙ አዛዦች በዚህ ወንጀል ተጠያቂ ከመሆን የሚያመልጡ አይመስሉም ሂዩማን ራይተስ ዎች ጉዳዩን በሰፊው ከመረመረ በኋላ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል ሂዩማን ራይትስ ዎች እንደሚለው የአገዛዙ አዛዦች በመራዊ በሰው ልጆች ላይ በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በህግ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ።
ሪፖርቱ እንደሚለው ጥር 20 2016 በመራዊ አደገኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል ከዚህ ውስጥም የ 26 አመት ወጣት ባሏ ፊት ለፊቷ መገደሉንና ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባት አረጋግጧል ገዳዮቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ እናት አቅፋው የነበረውን የሁለት ወር ህፃን በጥይት ሊመቱት እንደሞከሩ ሂዩማን ራይትስ ዎች ማረጋገጡን ይገልፃል።
ሆኖም እናት ተንበርክካ በመለመኗ ሳይተኩሱበት ሄደዋል በዚህና መሰል አጋጣሚዎች በሰው ልጆች ላይ ጅምላ ግድያ በመፈፀሙ የአገዛዙ ጦር አዛዦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል ሂዩማን ራይትስ ዎች ሁኔታውን በዚህ መንገድ ለአለም ቢያጋልጥም አገዛዙ ግን በመራዊ የተገደሉት ታጣቂዎች ብቻቸውን ናቸው በማለት መቀለዱ አይዘነጋም
ሂዩማን ራይትስ ዎች ግን በዚህ ብቻ አላበቃም የአገዛዙ ጦር ከተሰማራማባቸው አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪነት ስራው እንዲታገድም ጠይቋል።
በሌላ በኩል 42 ሀገራት የተካተቱበት የመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ በአማራ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከመቼውም ግዜ በላይ እንዳሳሰበው እስጠንቅቋል።
የብልፅግና አገዛዙ በፋኖ ላይ አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀመረ
አገዛዙ በፋኖ ላይ አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀመረ። የለገሰ ተሉ ፅህፈት ቤት ለአገዛዙ ልሳኖች ትእዛዝ አስተላልፏል።
በጦር ሜዳው ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰበት ያለው አገዛዙ ይህን ለማካካስ በፋኖ ላይ አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሊጀምር መሆኑ ተረጋግጧል።
ዛሬ ከለገሰ ቱሉ ፅህፈት ቤት የወጣው መመሪያ እንደሚያሳየው ከጥቂት ቀናት በኋላ የአገዛዙ ልሳኖች በፋኖ ላይ ዘመቻ እንዲጀምሩ የሚያደርግ ነው።
የዘመቻው ይዘት ፋኖ ከህዝብ ተነጥሏል አማራን በአማራ የመውጋት እቅዱ ስኬታማ ነው በአገዛዙ ዘመቻ ህብረተሰቡ ተሳታፊ ነው ከ12 ሺ በላይ ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል በቀጣይም ይሰጣሉ በፋኖ አመራሮች መካከልም ክፍፍል ተፈጥሯል የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል።
ይህም የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እስከ መጭው ማክሰኞ እንደሚጀመርም ተረጋግጧል አገዛዙ ከፋኖ በተጨማሪ በኦነግ ሸኔ ኤርትራ ግብፅ ላይም ተመሳሳይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንደሚጀምር የተገኘው ሰነድ ያመለክታል።
አገዛዙ በዚህ ደረጃ ፕሮፖጋንዳ ሲጀምር የመጀመሪያው ሲሆን ይህም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ አመላካች ነው።
የፋኖ የድል ውሎዎች
በግንደወይን ከተማ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሳሙኤል አወቀ ብርጌድ የተሳካ ኦፕሬሽን ማድረጉ ተገለጸ ።
በግንደወይን ከተማ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሳሙኤል አወቀ ብርጌድ በፋኖ ዳዊት የሚመራው ተወርዋሪው ጦር ድልን ተቀዳጅቷል ።
ካንብ መሽጎ የነበረውን የብልግና ሰራዊት ከከተማው ጠራርጎ በማስወጣት መሃል አደባባይ ደሴቱ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዱራ በኢትዮጰያ ህዝብ መዝሙር ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ውሏል ።
ፋኖ ከተማውን ሲቆጣጠር አንድ የቆሰለ ሲሆን በአገዛዙ ሰራዊት በኩል የታወቀ ነገር የለም።
ከተማ በምንቆጣጠርበት ሰአት ለድሮን ጥቃት ስለሚያጋልጠን እና ንፁሃን እንዳይጓድብን ባንዲራችንን ሰቅለን ከከተማው ዳር አለን ሲሉም ተናግረዋል።
ዘገባው የመታፈሪያ ሃይሌ ነው።
በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ መሽጎ የቆየው የአብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሽንፈት አጋጠመው::
በዚህም የአገዛዙ ወታደሮች ግማሹ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ቀሪው በምርኮና በሽሽት ህይወቱን ሊያተርፍ ችሏል። ድሉን የፈፀመው የምስራቅ አማራ ፋኖ የአሳምነው ክፍለጦር መሆኑም ታውቋል::
በሻለቃ በለጠ ሸጋውና በአማካሪው ኮሎኔል ሞገስ ዘገየና ኮሎኔል አባይ የሚመራው አሳምነው ክፍለ ጦር የገባውን ጥቁር ጣሊያን ወራሪ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ሮቢት ከተማን ለመቆጣጠር የመያስችሉትን ሰንሰለታማ ተራሮችን በተለምዶ አጤ አምባ ሶለላ አሮጌው ገብርኤል የሚባሉትን ተራሮች መቆጣጠር ችሏል።
ወራሪው ሀይል ፋኖን መቋቋም ሲያቅተው የንጹሀንን ቤትና ንብረት በከባድ መሳሪያ አውድማል
በተያያዘ ዜና በዋርካው ምሬ ወዳጆ ትዕዛዝ በሁለቱ ኮሎኔሎች የታቀደው ኦፕሬሽን በድል ተጠናቀቀ።
በሰሜን ወሎና በደቡብ ወሎ ዞኖች የሚንቀሳቀሰው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከቆቦ እስከ ሀይቅ እስቲፋኖስ ከፍተኛ ትንቅንድ ሲያደግ አርፍዷል።
በሰሜን ወሎ፦ሮቢት አጤ አምባ፥ሶለላ አጤ እርሻ፥ጎብዬ፥ብሆሮ፥ዶሮ ግብር፥መርሳ ፋጅና መነዮ ላይ በምድር ድሮኖቹ አሳምነው ክፍለጦርና አውጃኖ ከፍለጦር ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ገጥሞታል።
በዋርካው ምሬ ወዳጆ ትዕዛዝ በኮሎኔን ሞገስ ዘገዬና ኮሎኔል አባይ የታቀደው ኦፕሬሽን በስኬት በመጠናቀቁ የጥላትን ሀይል ማሳሳትና ማዳከም ብሎም ጥላት ያቀደውን የወሎን ሰንሰለያማ ተራራ የመያዝ ሴራ ማክሸፍ ተችሏል።
በደቡብ ወሎ፦ሃይቅ እስቲፋኖና ቢስጢማ ዙሪያው የባለሽርጡ ክፍለ ጦር የአብይ አህመድን ጽንፈኛና ገዳይ ቡድን የእንብርክክ ሲያስኬደው አርፍዷል።
ዛሬ በተደረጉ አውደ ውጊያዎች በርከት ያሉ የጦር መሳሪያዎችን ከጥላት ሀይል የተገኘ ሲሆን ሙትና ቁስለኛም በግፍ አስተናግዷል።
የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ ይህንን ጨፍጫፊና ተስፋፊ ሀይል አይቀጡ ቅጣት ሲቀራውና መቋቋም ሲያቅተው የንጹሀንን ቤትና ንብረት በከባድ መሳሪያ ሲጨፈጭፍ አርፍዷል።
ቸርነት ተሰማ (ከወሎ)
በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ጋይንት የአገዛዙ ወታደር ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ማስተናገዱ ተግልጿል።
በገብርየ ቅየ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ ምስለኔዉ የአገዛዙ ወታደር በገብርየ ልጆች ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።
መጋቢት 26/2016 ዓ/ም በታች ጋይንት ወረዳ ኤፍራታና አጋጣ ተብለዉ በሚጠሩ አካባቢዋች በተደረገዉ ትንቅንቅ ከሶስት ተሽከርካሪ በላይ የብርሀኑ ጁላ የመንደር ሚሊሻ ድል ተደርጓል።
የገብርየ ክፍለጦር በአገዛዙ ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱን የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ሻለቃ ከፍያለዉ ደሴ ለግዮን ሚዲያ ገልጿል።
በአካባቢው ሰፍሮ የነበረዉ የጠላት አብይ አህመድ ፀረ አማራዉ ምስለኔ ወታደር የፋኖን የበረታ ክንድ መቋቋም ስለተሳነዉ አካባቢዉን ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል።
በአሁኑ ሰአት የታች ጋይንት አጋጥ እና ኤፍራታ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባታቸዉም ተገልጿል።
በሻለቃ ከፍያለዉ ደሴ የሚመራዉ የገብርየ ክፍለጦር ከበሽሎ ወንዝ ተነስቶ የወረዳው መናገሻ የሆነችዉን አርገብያ ከተማን ለመቆጣጠር የ2 ኬሎሜትር ርቀት ብቻ እንደቀረም ዋና አዛዡ ለግዮን ገልጿል።
በዛሬዉ አዉደዉጊ የታች ጋይንት ወረዳ አርሶ አደር በአዉደዉጊያዉ ከልጆቹ ጋር በመሰለፍ የተለመደ ጀግንነቱን በአገዛዙ ወታደር ላይ አሳይቷል።
አዉደዉጊያዉ በአሁኑ ሳአት ተቀጣጥሎ የቀጠለ ሲሆን የጉና ክፍለጦር ከደብረታቦር ወሎ እንዲሁም ከእስቴ ስማዳ ጋይንት የሚያገናኘውን አዉራ ጎዳና ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ተጨማሪ የአገዛዙ ሀይል እንዳይገባ አድርጓል።
ቶማስ ፍትህ (ከጎንደር)
በጎንደር እና ጎጃም ተጨማሪ አዲስ ክፍለጦሮች ተመሰረቱ
በደቡብ ጎንደር ክፍለ ሀገር ተጨማሪ ክፍለጦር መመስረቱ ተገለፀ። በቀጠናዉ በስፉት ሲንቀሳቀስ የነበረዉ ጉና ክፍለጦር በፈጠረዉ አቅምና የሰራዉት እንዲሁም የትጥቅ ብዛት ተጨማሪ ክፍለጦር አዲመሰረት ምክናየት ሆኗል።
በቀጠናዉ የተመሰረተዉ አዲሱ ክፍለጦር ጀኔራል ነጋ ተገኘ ክፍለጦር የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ሲሆን በዉስጡ አራት ብርጌዶችን አቅፏል።
ክፍለጦሩ የአንዳቤት ብርጌድን፣የጣና ገላዉዲስ ብርጌድን፣የጋፋት ብርጌድን እንዲሁም የቤጌምድር ብርጌድን አካቶ በደብረታቦር፣በፎገራ፣በፋርጣ፣በአንዳቤት እንዲሁም በደራ ሀሙሲት በስፋት የሚንቀሳቀስ ነዉ።
የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ባለስናይፈሩ ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ ሲሆን ዛሬ መጋቤት 26/2016 ዓ/ም የክፍለጦሩን ምከትል አዛዥ ፣ፋይናንሰ፣የሎጀስቲክ ፣የሰዉ ሀብት አመራር፣ኦርዲናንስ፣የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ቃል አቀባይ በተዋረድ ምርጫ እያደረገ መሆኑን ዋና አዛዡ ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ ለግዮን ሚዲያው ገልጿል።
በተመሳሳይ የአማራ ፍኖ በጎጃም አራት ብርጌዶችን ያካተተ አዲስ ክፍለጦር ተመሰረተ ።
ክፍለጦሩ የባሶ ሊበኑ አብራጅት ብርጌድ ፣የአነደዱ ተድላ ጓሉ ብርጌድ ፣ የጎዛምኑ የየቦቅላ አባይ ብርጌድ ፣የአዋበሉ መብረቁ ብርጌድን ማካተቱ ታውቋል ።
የክፍለ ጦሩ ስያሜ የ3ተኛ(ሐምሌ 26)ክፍለ ጦር በሚል ተሰይሟል።
ይህን ክፍለ ጦር እንዲመሩ የተመረጡ አመራሮች ፦
1.ፋኖ ክንፈመላክ ካሳ — ሰብሳቢ
2.ፋኖ ትልቅዓለም አሳብ –ም/ሰብሳቢ
3.ፋኖ ዳበረ ይታየው — ፅ/ቤት ሃላፊ
- ፋኖ ግዛቸው መንበር– አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ
5.ፋኖ ላይችሉህ ገበየሁ — የህዝብ ግንኙነት
6.ፋኖ እንደሰው ታምሩ — ቀጠናዊ ትስስር
7.ፋኖ ኑርልኝ ምናለ — ፀጥታና ማህበራዊ ጉዳይ
- ፋኖ አንተናኔ ስንታየሁ — የፖለቲካ ዘርፍ
9.ፋኖ ይታያል ከበደ — የፍይናንስ ሃላፊ
10.ፋኖ ዶ.ር ደመቀ አያሌው –ጤና ዘርፍ
11.ፋኖ እንዳላመው ዘዉዴ —ኦርዲናንስ
12.ፋኖ ዶ.ር መቶ አለቃ ሀብታሙ ዘውዱ—ጦር አዛዥ
13.ፋኖ መቶ አለቃ አትፍራቸው ደረሰ—ም/ጦር አዛዥ
14.ፋኖ ደሳለኝ ዘውዱ — ዘመቻ መምሪያ
15.ፋኖ ምንያምር ሞላ — ሎጀስቲክስ ሃላፊ
16.ፋኖ ብዙዓለም ያደለው —አስተዳደር ሃላፊ
17.ፋኖ ሻበል ባተግዜ — ስልጠና መምሪያ ሃላፈ ሆነው ተመድበዋል ።
ዐብይ አሕመድ ወደ ባሕር ዳር እና መቀሌ ከተሞች ሊያመራ ማቀዱ ተሰማ
የአገዛዙ ቁንጮ ዐብይ አሕመድ ሕዝብን ለማወያየት በሚል ወደ ባሕር ዳር እና መቀሌ ከተሞች ሊያመራ ማቀዱን የግዮን ቴሌቭዥን ምንጮች ገለጹ።
ዐብይ አሕመድ ወደ ሁለቱ ከተሞች ሲያመራ ለውይይት የሚጋበዙ ሰዎች ከወዲሁ እየተመረጡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በስልጣን ዘመኑ በአማራም ሆነ በትግራይ በርካታ ሕዝብ እንዲጨፈጨፍ ያደረገው ዐብይ አሕመድ ወደ አካባቢው ሲያመራ ከአካባቢው ማህበረሰብ ተቃውሞ ሊገጥመው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህም ምክንያት የጸጥታ ጥበቃውን የአገዛዙ ወታደሮችና ልዩ ኮማንዶዎች ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በትግራይ በኩል የዐብይ አሕመድ ወደ መቀሌ መምጣትን ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ሊቃወመው ይችላል በሚል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እስካሁን ፈቃደኝነቱን አልገለጸም ተብሏል።
በአማራ በኩል ግን የባሕር ዳር እና የክልሉ ባለስልጣናት ተሳታፊዎችን ከተለያዩ አካባቢዎች በመምረጥ ሽር ጉድ እያሉ መሆናቸው ታውቋል።
ዐብይ አሕመድ ወደ ባሕር ዳር ሲያመራ አዲሱን የጎርጎራ ሪዞርት እግረ-መንገዱን ለማስመረቅ ዕቅድ መኖሩንም ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የአገዛዙ ሃይሎች ከአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ዘረፉ
የአገዛዙ ወታደሮች ዳንግላ ዙሪያ የአርሶአደሮችን ሁለት ተሳቢ የአፈር ማዳበሪያ ዘረፉ።
የዳንግላ ዙሪያ ወረዳ አርሶአደሮች አፈርማዳበሪያ እንዲገባላቸው ለህብረት ስራ ማህበራት ብር ሰብስበው ሰጥተዋል ።
በዚህም ገንዘቡ ተሰብስቦ ሁለት ተሳቢ የአፈር ማዳበሪያ ዳንግላ ከተማን አልፎ አቫድራ ሲደርስ የብልፅግና ሰራዊት በመዝረፍ ወደ መኮድ ማስገባቱ ታውቋል ።
በጎንደር ከ1 ሺ በላይ ዜጎች ታሰሩ
ሳንሰራ ግብር መክፈል እንችልም በማለታቸዉ ከ1 ሺ ባላይ ዜጎች መታሰራቸው ተገለፀ።
በደቡብ ጎንደር የመካነ እየሱስ ከተማ ኗሪዋች በአገዛዙ ታጣቂ ታፍሰዉ መታሰራቸዉን ኗሪዋቹ ገልጸዋል።
ላለፉት ስምንት ወራት ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ የቆዩት የመካነ እየሱስ ከተማ ኗሪዋች ዛሬም ከብልፅግና ታጣቂ ቡድን ጋር በስር ቤት ውስጥ ሆነዉ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ይገኛሉ።
የተደቀነባቸዉን የህልውና ትግል ለመቀልበስ ላለፉት ስምንት ወራቶች እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ ሲያደርጉ ቆይተዋል።የፖለቲካ አቅሙ ሙሉ ለሙሉ የተንኮታኮተው ብልፅግና በኢኮኖሚው ደግሞ ከፍተኛ ኪሳራ ገጥሞታል።
የኢኮኖሚ ኪሳራዉን ለማካካስ በአማራ ህዝብ ላይ በአምስት እጥፍ የተጠና ግብር እንዲከፍሉ በማድረግ የክልሉን ህዝብ በኢኮኖሚ ለማድቀቅ ግብር መክፈል የማይችሉትን በጀምላ እያፈሰ እስር ቤት ዉስጥ እያስገባ ይገኛል።
በእስቴ መካነ እየሱስ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዋች የተጣለባቸው ግብር ከአቅም በላይ በመሆኑ ከ1 ሺ በላይ ነጋዴዋች በሶስት ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረዉ ይገኛሉ።
ነገ ለምንሞተበት ዛሬ ግብር አንከፍልም፣አሁላይ የምንከፍለዉ ግብር ለብልፅግና ወታደር ደሞወዝ እና መሳርያ ግዥ እንዲዉል እንጅ ለህዝቡ መሠረተ ልማት ታስቦ ባለመሆኑ ሞታችን እስር ቤት ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ይፋረደን ሲሉ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሳአት በከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተቆረጠ ሲሆን ሆቴሎች፣ታላላቅ ሱቆች፣መጋዘኖች ከተዘጉ ዛሬ አምስተኛ ቀናቸዉን አስቆጥረዋል።
ዛሬም የአገዛዙ ሚሊሻ በመንገድ ላይ ያገኛዉን ወጣት እያፈሰ ግብር ትከፍላለህ በማለት ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራ እያሳደረ እንደሚገኝም ቶማስ ፍትህ ከጎንደር የላከልን ዘገባ ያሳያል።
በተመሳሳይ የአገዛዙ ኃይሎች በደቡብ ወሎ እና በሰሜን ወሎ ዞኖች በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ወጣቶችን በማገት “ምርኮኛ ፋኖ ናቸው” በሚል በቪድዮ ቀረፃ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
በጉልበት ስራ ላይ እንዳሉ በአገዛዙ ወታደሮች የታፈኑት ወጣቶች በሲኖ ትራክና በኤፍ ኤስ አረ ተጭነው ተወስደዋል።ሰሞኑን በሁለቱ ዞኖች በነበረ ውጊያ የተማረኩ ናቸው በሚል ተገደው በቪድዮ እንዲቀረፁ መደረጋቸው ነው የተነገረው።
የስርዓቱ አገልጋዮች የጉልበት ሰራተኞቹን በቀረፃ ወቅት ማለት ያለባቸውን አስገድደው እንዳስጠኗቸውና አንልም ያሉ ወጣቶችን ደግሞ በከባድ ሁኔታ መደብደባቸውን ነው የአይን እማኞች የገለፁት።
የተቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስል ዛሬ ማታ ወይንም ነገ አገዛዙ በሚዘውራቸው ሚድያዎች በኩል ሊሰራጭ እንደሚችል ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ስለሆነም የስርአቱ አገልጋዮች ማሕበረሰቡን ለማደናገር ይሄንን የሀሰት መረጃ ከማሰራጨታቸው አስቀድሞ ማጋለጥ እንደሚገባም ምንጮቻችን አሳስበዋል።
በአሜሪካ የጸሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄው
በአሜሪካ የተወሰኑ አካባቢዎች ሙሉ የጸሐይ ግርዶሽ እንደሚኖር የመስኩ ባለሙያዎች ገለጹ።
ሲኤንኤን እንደዘገበው በተለይ ከቴክሳስ ጀምሮ ወደ ደቡባዊ ምስራቅ አቅጣጫ እስከ ኒዮርክ ድረስ ሙሉ የጸሐይ ግርዶሽ ይከሰታል።
ይህን በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ ሊያጋጥም ይችላል የተባለው ሙሉ የጸሐይ ግርዶሽ 32 ሚልዮን አሜሪካዊያን የማየት ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
በተወሰኑ ቦታዎች በጸሐይ ግርዶሹ ምክንያት ቀኑ ወደ ጨለማነት ሊቀየር እንደሚችልም ነው የተዘገበው።
ግርዶሹን ለማየት አራት ሚልዮን ቱሪስቶች ይሕ ክስተት ወደሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ያመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመልክቷል።
ዓይንን ከጉዳት በመከላከል የጸሐይ ግርዶሹን ለመመልከት የሚያስችሉ ልዩ መነጽሮች ገበያ ላይ መሆናችውንም ለማወቅ ተችሏል።