LOADING...

GTV

Trending Today
April 8, 2024

ዕለታዊ ዜናዎች መጋቢት 30/2016 ዓ.ም

By

በወልድያ ከተማ  የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ

የሰሜን ወሎ ዞን መናገሻ በሆነችው ወልድያ ከተማ የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የቦምብ ፍንዳታዎቹ የተፈጸሙት በከተማዋ የተላያዩ አካባቢዎች መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የብልጽግና ምስለኔ የሆኑ የብአዴን ካድሬዎች ለዛሬ መጋቢት 30 የከተማዋን ማሕበረሰብ አገዛዙን በግድ ደግፉ  በሚል ሰልፍ ሊያካሂዱ እንደነበር  ለመርዳት ተችሏል።

ይህ ከሆነ ሰልፉን ባስተባበሩ ካድሬዎችና በሰልፉ ታዳሚዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰዱ የምስራቅ አማራ ፋኖ እዝ የማስጠንቀቂያ መገለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም።

በዚሁ መግለጫም የከተማዋ ማሕበረሰብ በሰልፉ ባለመሳተፍ እራሱን እንዲጠብቅ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፎ ነበር።

ይህንኑ ተከትሎም በወልድያ ከተማ ጎንደር በር አደባባይ፣  ውሃ ልማት ፖሊስ ጣቢያ፣  ጎማጣ ፖሊስ ጣቢያ፣  አዳጎ አደባባይ እና አዳጎ ፖሊስ ጣቢያ ላይ  መጋቢት 29 /2016 ከለሊት ጀምሮ እሰከ ማለዳ ተደጋጋሚ የሆነ የቦምብ ፍንዳታ መፈጸሙን ነዋሪዎች ለግዮን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

በዚሁ ዕለት የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ታዲያ ሰልፉን ለማካሄድ ለሚወጡ ባንዳዎች ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሆኑን   የከተማዋ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በቦምብ ፍንዳታው የተጎዳ ሰውና ንብረት ስለመኖሩ እስካሁን በውል የታወቀ ነገር የለም።

 

በባህርዳር የአገዛዙ ታጣቂዎች በሙስሊሞች ላይ ጥቃት በመፈጸም የአንድ ቤተሰብ አባላትን መግደላቸው ተሰማ

በወለጋ ሻንቡ ከተማ 28 አማራ ሙስሊሞች በአሰቃቂ ሁኔታ በኦነግ ሸኔ ተገደሉ።

በተመሳሳይ በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቻቸው ጋር ተገደልዋል። በዚሁ ጥቃት አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ በአጠቃላይ 5 ሰዎች በአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ነው የተነገረው ።

መጋቢት 29/2016  በግፍ የተገደሉት እራሳቸው አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና  አቶ እንድሪስ የተባሉ ጎረቤታቸው መሆናቸውን ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል።  ቀብራቸውም በማግስቱ ተፈፅሟል።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበትም ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና የአገዛዙ ስራዊት ሰሞኑን በሰሜንና ደቡብ ወሎ ንፁሃን ላይ ግድያ እና አሰቃቂ ግፎችን እየፈፀመ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

የፋኖን ብርቱ ክንድ መቋቋም የተሳነው ይህ የብልጽግና ሰራዊት የፋኖንና የአማራን ልዩ ሃይል መለዮ ልብስ በመልበስ ነው ግድያ እየፈፀሙ የሚገኙት::

በእዚህም የጎልቦ ሚካኤል አገልጋይ  የነበረ ተስፋይ ከበደ የተባለ አንድ ዲያቆን በአገዛዙ ሰራዊት በግፍ ተገሏል::

የአይን እማኞች ለግዮን ቴሌቭዥን እንደተናገሩት ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያን ዘግቶ በመውጣት ላይ ሳለ ነው ጭንቅላቱ ላይ ተኩሰው በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉት::

በተመሳሳይ በመርሳና ውጫሌ መካከል በምትገኝ ወርጌሳ በምትባል ቀበሌ አንድን ግለሰብ በእሾህ ገርፈው ራሱን እንዲስት ካደረጉ በህላ ወደራሳቸው ካምፕ በመውሰድ እንደገደሉት  ታውቋል።  አስክሬኑን ማንም እንዳይነካ በመከልከልም ጅብ እንዳስበሉት በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ቸርነት ተሰማ የላከልን ዘገባ ያመለክታል።

በተጨማሪም በጊራና ልዮ ስሙ መነዮ በተባለ አካባቢ አንድ የመስጊድ ኢማም ፋኖን ትደግፋለህ በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሏል::

በሌላ በኩል በሮቢት ከተማ እነዚህ ሰራዊቶች 3 ንፁሃን ወጣቶች ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ድብደባ ወጣቶቹ በህይወት እና በሞት መካከል ናቸዉ ተብሏል:: በዚሁ በሮቢት ከተማ አንድ ባለሃብት ቤት በመግባትም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ አገኘን በሚል ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውበታል:: የግለሰቡን የውስጥ እግር ክፉኛ በመጉዳት ከዚያም አፍነው እያሰቃዩ ወደ ሮቢት ስላሴ እንደወሰዱት ነው የተነገረው::

 

 

በሰሜን ጎንደር ዞን የምስራቅ ጠለምት እና ማይጠምሪ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በሰሜን ጎንደር ዞን የምስራቅ ጠለምት እና ማይጠምሪ ነዋሪዎች “አማራ ነን እንጂ፤አማራ እንሁን አላልንም!” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፉ የተካሄደው ብልፅግናና ህወሃት በወልቃይት፣ በራያና ጠለምት ያሉ የአማራ አስተዳደሮችን በማፍረስ ለትግራይ ክልል ሊያስረክቡ ሰሞኑን ወስነዋል መባሉን ተከትሎ ነው።

በሰልፉ የጠለምት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ነጋ ካሳና አባላቱ የተገኙ ሲሆን በሕዝባዊ ሰልፉም የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በዚህም “የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው፣ አማራዊ ማንነታችንና የወሰን አስተዳደር ግዛት በሕግ አግባብ ይከበር፣ ጠለምት ላይ ተቀምጦ ሽብር እየፈጠረ ያለው የሕውሃት ታጣቂ ከክልላችን ይውጣ፣ መንግስት በጀታችን ይልቀቅልን” የሚሉ ይገኙበታል።

ባለፈው ሳምንትም የራያ አካባቢ ነዋሪዎች በተመሳስይ ሁኔታ ዳግም የአማራ ማንነት ጥያቄያቸው እንዲታፈን መደረጉን መግለጻቸው ይታወሳል። በዚሁም አገዛዙ ሕዝብን ያለፍላጎቱ ማንነቱን እንዲቀይር ለማስገደድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል።

በጎጃም እንጅባራ ከተማ  በመካሂድ ላይ የነበረው የብልጽግና የድጋፍ ሰልፍ ተቋረጠ

በአገው ምድር እንጅባራ ከተማ  መጋቢት 30/2016 ዓ/ም በመካሂድ ላይ የነበረው የብልጽግና የድጋፍ ሰልፍ የአማራ ፋኖ በጎጃም በወሰደው እርምጃ ተቋረጠ።

ሰልፉን ሲያስተባብሩ የነበሩት የብልጽግና ካድሪዎችን በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንደሆኑ ነው ዘጋቢያችን መታፈሪያ ሃይሌ የላከልን ዘገባ የሚያስረዳው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር እንጂባራ ዙሪያ ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር እየተፋለመ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

 

 

 

ህውሓት በሰቆጣ በኩል ዳግም ተኩስ ጀመረ

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን እና አካባቢው በሚገኙ አበርገሌና ጻግብጅ  ወረዳዎች ላይ ነው ከሰሞኑ ህውሃት ጦርነት የከፈተው።

ህውሃት ጦርነቱን የጀመረው በአካባቢው ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮቸና ሚኒሻዎች ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ጥቃቱን ተከትሎ ወታደሮቸና ሚኒሻዎች በድንጋጤ አካባቢውን ፈጥነው በመልቀቃቸው ጦርነቱ ወደ ነዋሪው ህዝብ ተዛምቷል። በዚህም ነዋሪው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል:፡

የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት  ሽመልስ አብዲሳ በቅርቡ ወደ ስፈራው አምርቶ ነዋሪዎችን ሰብስቦ እንደነበር ነዋሪዎች ለግዮን ቴለቪዥን  ተናግረዋል.።

በዚህም በሰቆጣ እና አካባቢው ያላችሁ ሰዎች አገው ስለሆናችሁ በአማራ እየተገደላችሁ ነው የሚል ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ፀብ አጫሪ ንግግር አድርጎ እንደተመለሰም ለማረጋገጥ ተችሏል::

በሰሜን ጎንደር ዞን የምስራቅ ጠለምት እና ማይጠምሪ ነዋሪዎች “አማራ ነን እንጂ፤አማራ እንሁን አላልንም!” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፉ የተካሄደው ብልፅግናና ህወሃት በወልቃይት፣ በራያና ጠለምት ያሉ የአማራ አስተዳደሮችን በማፍረስ ለትግራይ ክልል ሊያስረክቡ ሰሞኑን ወስነዋል መባሉን ተከትሎ ነው።

በሰልፉ የጠለምት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ነጋ ካሳና አባላቱ የተገኙ ሲሆን በሕዝባዊ ሰልፉም የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በዚህም “የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው፣ አማራዊ ማንነታችንና የወሰን አስተዳደር ግዛት በሕግ አግባብ ይከበር፣ ጠለምት ላይ ተቀምጦ ሽብር እየፈጠረ ያለው የሕውሃት ታጣቂ ከክልላችን ይውጣ፣ መንግስት በጀታችን ይልቀቅልን” የሚሉ ይገኙበታል።

ባለፈው ሳምንትም የራያ አካባቢ ነዋሪዎች በተመሳስይ ሁኔታ ዳግም የአማራ ማንነት ጥያቄያቸው እንዲታፈን መደረጉን መግለጻቸው ይታወሳል። በዚሁም አገዛዙ ሕዝብን ያለፍላጎቱ ማንነቱን እንዲቀይር ለማስገደድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል።

 

 

 

 

የምስራቅ አማራ ፋኖ ዘጠነኛ ዙር ሰልጣኞችን አስመረቀ

በኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይ የሰለጠኑት እነዚህ ተመራቂዎቸ ከዚህ ቀደም ከሰለጠኑት 8 ዙር ሰልጣኞች በተለየ ልዩ የኮማንዶ ስልጠና እንደወሰዱ በምረቃው ዕለት ተገልጿል:: በዚህም እስካሁን ከነበረው የሽምቅ ውጊያ ባሻገር የፊት ለፊትና የከተማ ዉጊያዎቸ ለማድረግ በስልጠናው ከፍተኛ ብቃት አግኝተዋል ተብሏል::

የምስራቅ አማራ ፋኖ እዝ ዘመቻ ሃላፊ ጌታቸው መልኩ ተመራቂዎች ከተማ ገብተው ጠላትን ማጥቃት ብቻ ዒላማ አርግው እንዲዋጉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ተመራቂዎች  የህዝብ ሃብትና ንብረት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን እንዲጠብቁ ሃላፊው አደራ ብለዋል።

ተመራቂዎቸ በምስራቅ አማራ ፋኖ ተሰልፈው ሲዋጉ የተሰው ፋኖ አለሙ ከበደ፣ ዳንኤል አለሙ እና  ሌሎችንም በትግሉ ያለፉ ፋኖዎቸን በማስታዎስ ትግሉን በጠነከረ መልኩ  ለማስቀጠል እና አደራቸውን ለመፈፀም ቃል ገብተዋል። በቅርቡ የተሰዋውን የታጋይ ዉባንተን ቲሸርት በመለበስም የተሰው ጀግኖችን ዘክርዋል።

አንድ የአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት ፕሮፌሰር አብይ አህመድን ተቹ

የአገዛዙ ቁንጮ የምጣኔ ሀብት እውቀት የሌለውና ህዝቡንም ድህነትን እያለማመደው ይገኛል  ሲሉ አንድ የአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ የምጣኔ የሀብት ፕሮፌሰር ተቹ ።

ግዮን ቴሌቪዥን ከብሄራዊ ባንክ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሠረት አገዛዙ ብር በማተም ተግባር ላይ ተጠምዷል።

 

የአገዛዙ ቁንጮ የምጣኔ ሀብት እውቀታቸው እዚህ ግባ የማይባል ነው በማለት ብዙዎች ይተቻሉ።  ሰውየው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ትንታኔን ከመስጠት ይልቅ ሙዝ በዳቦ ብሉ ቂጣ በጎመን በልተን ነው ያደግነው፥ ድህነት አዲስ ነገር ነው ወይ ፥ የሚሉ ተራ እና አሰልቺ ትንታኔዎችን ሲሰጡ መስማት የተለመደ ነው።

በዚህም ብቻ ሳያበቃ ሰውየው በምጣኔ ሀብት  ዙሪያ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ሀሳብ ለመስጠት ፈርተው ተቀምጠዋል።

እናም ብዙዎች እንደሚሉት ሀገሪቱ እየተመራች ያለችው እውቀት አጠር በሆነ ግለሰብ ነው።

ይህንን በተመለከተ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት ፕሮፌሰር የአገዛዙ ቁንጮ በዘፈቀደ ሀገሪቱን እየመራት ነው ሲሉ ይተቻሉ ፡፡

ሰውየው መሠረታዊ የምጣኔ ሀብት እውቀት ያለው ስለመሆኑ እንደሚጠራጠሩም አልሸሸጉም። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት የህዝብን ህይወት የሚቀይሩ ስራዎች እንዲቆሙ ተደርገዋል። በምትካቸውም ፓርኮችና ቢሮዎች እድሳት  ላይ በቢልዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ይፈሳል ፥ ገንዘብ የሚወጣውም ህገ ወጥ በሆነ መንገድ መሆኑን የሚገልፁት ፕሮፌሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ጉዳዩ ሲጠየቅ አያገባችሁም የሚል መልስ መስጠቱ  የሀገሪቷን የቁልቁለት ጉዞን እንደሚያፋጥነው ያብራራሉ። የአገዛዙ ቁንጮ በዚህ ብቻ ሳያበቃም የተከለውን  ዛፍ ሜጋ ፕሮጀክት ነው እያለ  ለአለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ሲያሳይ  እፍረትም  አይሰማውም  በማለት ፕሮፌሰሩ አጣጥለውታል። ከዛም ጎን ለጎን ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ዙሪያ ሲጠይቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሳለቅና ይህም እውቀት አጠር መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በስንት ፐርሰንት አደገ የሚል ክርክር ነበር። አሁን ግን ይህ ሀሳብ ተረስቶ 30 ሚልየን ህዝብ ለምግብ ተረጅነት ተጋልጧል ብለዋልል። እንደ ምሁሩ ገለጻ  ኢኮኖሚው በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የውጭ ምንዛሬ ክምችቱም ከግዜ ወደ ግዜ እየተመናመነ ነው  ።

እናም አገዛዙ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ብር በማተምና ወደ ሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ በማስገባት ስራዎች ላይ መጠመዱን ግዮን ቴሌቪዥን ከብሄራዊ ባንክ የውስጥ ምንጮች ያገኘው መረጃ ያረጋግጣል።

 

Prev Post

የዕለቱ ዜናዎች

Next Post

ዕለታዊ ዜናዎች

post-bars

Leave a Comment