ዕለታዊ ዜናዎች
ሚያዝያ 02/2016 ዓም በአዊ ዞን አዮ ምሬት ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከጠዋቱ 1:00 እስከ 7:00 በነበረ አውደውጊያ የጠላት ወራሪ የሽብር ኃይል ብትንትኑ መውጣቱ ታወቀ።
በዚህ አውደውጊያ የእሁዲት አካል ብርጌድና የጓጉሳ ብርጌድ ከወገን በኩል ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን የወገን ኃይል በድል መንበሻበሹን የአካል ብርጌድ አዛዥ ሻለቃ በላይ ዘለቀ ለባህርዳር ዊክሊክስ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።
በነበረው ውጊያ 83 ያህል የአራዊት ሰራዊቱ ከምድር በታች መሆኑ የታወቀ ሲሆን 80 ያህል ደግሞ ክራንች አንጋች እንዲሆን መደረጉ ተነግሯል።
በተጨማሪም በርካታ ቁጥር ያለው ጥቁር ክላሽ ለወገን ኃይል ገቢ መደረጉም ታውቋል።
ከዚህ አውደውጊያ በህይወት የተረፈው ወራሪ ኃይል ነቅሎ ወደ አዘና ከተማ ማፈግፈጉንም የአካባቢው ምንጮች ጠቅሰዋል።
ዘገባውን ከስፍራው ያደረሰን ባልደረባችን መታፈሪያ ሀይሌ ነው።
========//////////========
በተያያዘ ሚያዝያ 01 ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት በተደረጉ ጦርነትቶች ድል መመገባቸውን የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ልዩ ልዩ ብርጌዶች አስታወቁ።
በደብረ ብርሃን ጠባሴ ክፋለ ከተማ ጎሾባዶ በሚባል ቦታ በፋኖና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል በተደረገ ዉጊያ የአገዛዙ ቡድን ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
የአማራ ፋኖ ሽዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፋለጦር አንበሳው ብርጌድ አስራት ሻለቃ እና ባሩድ ሻለቃ ከፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራው) ክፋለጦር አርበኛ አሊ ሻለቃ ጋር በጋራ በመቀናጀት ድሉን አፋጥነውታል።
ሙትና ቁስለኛ የሆነው የአገዛዙ ሰራዊትም ቁስለኛውን እያጋዘ እሬሳውንም እየጣለ መፈርጠጡ ታውቋል።
የአማራ ፋኖ ሽዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር አንበሳው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ በደብርብርሃን ጣይቱ ክፋለ ከተማ ዘንደጉር እና ቀይት በተባለ የተለያዩ ቦታወች የአገዛዙን ጥምር ጦር ተብሎ የሚጠራውን ቡድን በቆረጣ ብትንትኑን በማውጣት አናብስቶቹ ጠላትን እንደቅጠል አርግፈውታል።
ሚንሊክ ክፈለ ከተማ ወሻውሽኝ በሚባል ቦታም ነጎድጓድ ክፈለጦር ጋተው ብርጌድ የአገዛዙን ጥምር ጦር ቡድን በድንገት ሲመታ ጦሩ ፈርጥጦ ደብርብርሃን ከተማ ውስጥ ጎብቷል።
አናብስቶቹም ለከተማቸውና ለህዝባቸው ደህንነት ወደ ኋላ በመውጣት በከተማው ጫፍ ሰፍረዋል።
አናብስቶቹ ህዝባችን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበን በቀጣይ በምናደርገው የከተማ የሽምቅ ውጊያ የአገዛዙን ተላላኪ ጦር የምንደመስሰው ይሆናል ብለዋል።
የአማራ ፋኖ ሽዋ እዝ መብረቁ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00 ስአት በሞጃና ወደራ ወረዳ ሰላድንጋይ ከተማ የማጥቃት ውጊያ ያደረገ ሲሆን ውጊያው ይህ ዘገባ እስከተሰራበት ስአት ጠላትን መውጫ መግቢያ እሳጥቶታል።
በቡዙ አቅጣጫ የተመታው የአገዛዙ ሰራዊት በሁሉም አውደ ውጊያወች ክፉኛ በመመታቱ ለበቀል መወጫ በሚል በአካባቢው ባሉ ሚሊሻ መሪነት የፋኖ ቤተሰብ እና የፋኖ የብርጌድ አመራር የሆነውን የ፶/አ አዝማድ ከበደ የመኖሪያ ቤትን አቃጥሏል።
አናብስቶቹ በበኩላቸው የአገዛዙ ጦር አቅመ ቢስ መሆኑን እና መፈርክርኩን ያየንበት ድል ነው ያስመዘገብነው ሲሉ የአውደ ውጊያ ውሏቸውን ገልጸውታል።
ዘገባውን ከስፍራው የላከልን ባልደረባችን በቃሉ ደረሰ ነው።
========//////////========
ኤርትራ ሁለት የትግራይ ግዛቶችን መቆጣጠሯ ተሰምቷል።
በአሁኑ ሰአት የኢሳያስ አፈወርቂ ጦር ዛላንበሳ ድረስ ዘልቆ መግባቱም ታዉቋል።
የኤርትራ ጦር ኢሮፕ የተባለዉን የትግራይ ግዛትን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዋ አስተዳደር አቶ ጌታቸዉ ረዳ የኤርትራ ጦር የትግራይ ግዛትን መቆጣጠሩን ለፌደራል መንግስቱ አስታዉቋል።
የትግራይ ግዛቶች ባልሆኑት በአማራ ግዛቶች ራያ አላማጣ እና ወልቃይት ጦር ለማዝመት ሙከራ እያደረገ የሚገኛዉ ህወሓት በኤርትራ በኩል የራሱን ግዛት አሳልፎ ሰጥቷል።
የኢሳያስ አፈወርቂ ጦር ከኤርትራ ጋር የሚዋሰኑ የትግራይ ወረዳዋችን በብዛት ተቆጣጥሯል።
ጦሩ ዛሬም በዛላንበሳ በኩል ከ12 ኪሎሜትር በላይ ቦታዋችን ተቆጣጥሮ መዋሉን የዛላንበሳ ከተማ ኗሪዋች ለግዮን ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የሀገሪቱን ሉኣላዊነት እያስደፈረ ያለዉ አገዛዙ የኤርትራ ጦር ኢሮፕን መያዙን ከሰማ በኋላ ወታደራዊ መኮንኖችን ስብሰባ ጠርቷል።
ከ50 ሺ ያልበለጠ ሰራዉት ያለዉ አገዛዙ በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ያልጠበቀዉ ከባድ ፈተና ተደቅኖበታል።
ከአማራ ህዝብ ውጭ እንደማይሳካለት የሚታወቀዉ አፈ ቀላጤው አብይ አህመድ ኤርትራ በዚህ ከቀጠለች የኢትዮጵያ የመፈራረስ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይደርሳል።
የምስራቅ አፍሪካን የተረጋጋ ፖለቲካ በማፈራረስ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣለው አብይ አህመድ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የሚገጥም ከሆነ ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷ የማይቀር ጉዳይ ነዉ።
ከብዙ ጭንቅ ያተረፈውን ፋኖ እየተዋጋ ሀገር እገነባለዉ ማለት የህልም ቅዥት መሆኑን የተረዳዉ ምስለኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገሪቱን አደጋ ውስጥ ከቷታል።
የኤርትራ ጦር አዲግራት ከተማ ለመግባት በቅርብ ርቀት ላይ መሆኑም ተረጋግጧል።
ዘገባውን ባልደረባችን ቶማስ ፍትህ አድርሶናል።
========//////////========
የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል በቴ ኡርጌሳ ሆቴል ውስጥ ሞተው ተገኙ።
በቅርቡ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የኦነጉ ከፍተኛ አመራር ጃል በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ከተማቸው መቂ ከተማ ነው የተገደሉት።
አገዛዙን በመቃወም እና በአገዛዙ ቁንጮ ላይ ትችቶችን በማቅረብ የሚታወቁት እኚህ ግለሰብ የሞቱበት ምክንያት አልታወቀም።
ይህም ቢሆን ግን የሰውየው ግድያ ሆን ተብሎ በአገዛዙ የተቀነባበረ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ለግዮን ቴቪ ተናግረዋል።
ግለሰቡ በቅርቡ ከአንድ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገሀል ተብሎ በአገዛዙ ታስሮ እንደነበረም አይዘነጋም።
ሆኖም በአንድ መቶ ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ከተደረገ ከቀናት በኋላ ህይወቱ አልፏል።
አገዛዙም ሆነ ፓርቲያቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰሩን ግድያ በተመለከተ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
========//////////========
በመንግስት አካላት የሚዘወሩ የሀይማኖት አባቶች በክልሉ ላይ ተጨማሪ ስጋትን እየደቀኑ መሆናቸው ተገለፀ።
ሰሞኑን በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር በተፈፀመ ግድያ የሀይማኖት አባቶች የመንግስትን አጀንዳ ተቀብለዉ በየአደባባዩ የሚያደርጉት ንግግር ለሰላማዊ ዜጎች የማይበጅ ነው ሲሉ 1445ኛዉን የኢድ አልፈጥር በአል የታደሙ የጎንደር ከተማ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ለግዮን ሚዲያ ተናግረዋል።
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች መሰል ድርጊቶች ሲፈጸሙ ዝምታን የመረጡ አካላት የአማራ ክልሉን ግድያ ከሃይማኖት ጋር አያይዘው ሊያቀርቡ የሞከሩበትን አጀንዳ መመርመር ይገባል ሲሉም ለግዮን ሳተላይት ቴሌሺዥን ተናግረዋል።
ዘገባውን ባልደረባችን ቶማስ ፍትህ ከስፍራው አድርሶናል።
========//////////========
በጋምቤላ እየተፈጠረው ላለው የፀጥታ አለመረጋጋትና ግጭት ተጠያቂዎቹ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች ናቸው ተባለ።
ሪፖርተር ጋዜጣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕነን) ሊቀመንበር አቶ ሳይመን ቱትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከ2015 ዓ.ም.
Melkam Anteneh, [4/10/2024 10:01 PM]
ወዲህ በጋምቤላ ክልል ውስጥ አለመረጋጋትና ግጭት እየተባባሰ ነው።
ለዚህ ደግሞ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች በክልሉ ውስጥ ከሚነቀሳቀሱ ኢመደበኛ ከሆኑ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር በመሆን ሰላም እያደፈረሱ መሆናቸውን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሳይመን ፅንፈኛ ኃይሎች ያሏቸውን ማንነት በስምም ሆነ በወል አልገለጹም::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. በክልሉ እየተባባሰ ስለመጣው ግጭት ዋነኛ ምክንያት ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን ድንበር አቋርጠው የሚመጡ የታጠቁ የኑዌር ኃይሎች በስደተኝነት ሠፍረው ከሚገኙ ኑዌሮች ጋር በመተባበር በአኝዋክ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነ ነበር ኢሰመጉ በሪፖርቱ የገለፀው:: ይህን ሪፖርት ግን አቶ ሳይመን ‹‹የሐሰት ውንጀላ›› ብለውታል፡፡
ከደቡብ ሱዳን የመጡት ስደተኞች ኑዌር ናቸው ስለተባለ ብቻ የግጭቱ ፈጣሪ ኑዌር ነው የሚለው ክስ ተቀባይነት የለውም፡፡
ይልቁንም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች ናችው በሁለቱ ብሔረሰቦች ውስጥ ተደብቀው ግጭት እየፈጠሩ የሚገኙት፡፡ ይህም ማለት የችግሩ ፈጣሪ እየታወቀ ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ አለመሰጠቱ ከጀርባው ማን እንዳለ ግልጽ ያደርገዋል ብለዋል ሊቀመንበሩ።
በቀደሙት ጊዜያት ሁለቱ ብሔረሰቦች በከብቶች ውኃና ግጦሽ ምክንያት የሚጋጩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ ነገር ግን ግጭቶቹ እዚህ ግባ የማይባሉና በአካባቢው ባሉ የአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች ወዲያውኑ የሚፈቱ እንደነበሩም ሊቀመንብሩ ገልጸዋል።
አሁን የሚታየው ግጭት ግን ሁለቱን ብሄረሰቦች እርስ በርስ ለማጨራረስ የሚያደርስ እና አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሻም ገልጸዋል::
========//////////========
በአሁኑ ሰአት እንደ አማራ ግፍ የሚያሰተናግድ ህዝብ በየትኛውም የአለም ክፍል አይገኝም ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሰብአዊ መብት ሰራተኛ ለግዮን ቴሌቪዥን ተናገሩ።
በኢትዮጵያ አማራ መሆን ወንጀለኛ ተደርጎ ይቆጠራል ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የአብይ አህመድ አስተዳደር ሰሞኑን በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ወሊሶ አመያ ወረዳ እና አጎራባች ወረዳዋች በአማራዎች ላይ የማንነት ተኮር ጥቃት ተፈፅሞ ከ78 በላይ አማራዋች ሲገደሉ ዝምታን መርጧል ብለዋል።
በዚህ ዞን አጎራባች ምዕራብ ሸዋ ዞን ስልክ አምባ ወረዳ 39 አማራዎች እንዲሁም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣በምራብ ወለጋ ቁጥራቸዉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎችም ተገድለዋል ብለዋል።
በአብይ አህመድ አስተዳደር አማራን የሚያሳድድ ግለሰብም ሆነ ቡድን የተለየ ክብር ይሰጠዋል ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት እኚህ የሰብአዊ መብት ሰራተኛ ይህን ድርጊት የሚያበረታታ ሁሉ በመንግስት በኩል የበጀት ድጎማ ይደረግለታልም ብለዋል።
የሰብአዊ መብት ሰራተኛዉ በአማራ ክልል መላ ጎንደር፣ በባህርዳር ፣ እንዲሁም በመዲናዋ አቅራቢያ መራዊ በመንግስት የተፈፀሙ ግድያዎችን ተመልክቻለሁ በማለትም ጉዳዩን አብራርተዋል።
በጎንደር ከተማ ከዚህ በፊት በተደረገ አራት ጦርነት በመንግስት ታጣቂዋች ከ175 በላይ ምዕመናን ፣ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ መሎ ሰፈር አቡዬ ቤቴክርስቲያን 5 ንፁሀን ዜጎች በሞርታር፣ በእስቴ መካነ አየሱስ፣ በአንዳ ቤት፣ በደራ ሀሙሲት፣ በፋርጣ፣ በጋይንት፣ በእብናት፣ በመና መቀጠዋ፣ በስማዳ ሰዴ ሙጃ፣ በሊቦ ከምከም፣ በደንቢያ፣ በበለሳ፣ በአርማጭሆ፣ በአጅሬ ጃኖራ ፣በዳባት ገደብየ፣ በደባርቅ አንባ ጌዮርጊስ፣ በቋራ መተማ፣ በማክሰኝት ፀዳ እና አዘዞ ብቻ ከ880 በላይ ምዕመናን ሲገደሉ ሰልፍ ወቶ ያወገዘ ማንም አካል አለመኖሩ እንዲሁም አንድም የመንግስት ሚዲያ ምንም ያለዉ ነገር አለመኖሩ ሞት ለኦርቶደክስ እምነት ተከታዮች ብቻ መስሎ እስኪታይ ድረስ የአብይ አህመድ ወታደር ግፍ ሲፈፅም ታዝቤያለሁ ሲሉም የሰብአዊ መብት ሰራተኛዉ ከግዮን ሳተላይት ቴሌሺዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በጎንደር ከ560 በላይ የቆሎ ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን በመንግስት ሀይል ተገደዉ ወደ ዉትድርና ማሰልጠኛ ሲወሰዱም ሁሉም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ያለፈው ጉዳይ ነውም ብለዋል።
በጎንደር 303 አርሶ አደሮች ሞፈር ቀንበር እንደተሸከሙ በአገዛዙ ወታደር ሲገደሉ አርሶ አደር ተገደለ ብሎ ያወገዘ ማንም አለመኖሩም በአማራ ላይ የሞት ማዕቀብ መጣሉን በግልፅ ያየንበት ነውም ብለዋል።
እጅግ በርካታ ግድያ በአማራ ክልል በመንግስት ሃይሎች ሲደረግ ፀጥ ረጭ ያለ ሚዲያ ሰሞኑን መንግስት እራሱ በሰራው የሴራ ፓለቲካ ፅንፈኛ የሀይማኖት አባቶችን በመያዝ በክልሉ ህዝብ ላይ ሀይማኖታዊ ግጭት ለመፍጠር ግፊት እያደረገ መሆኑንም ታዝቢያለሁ ሲሉ የሰብአዊ መብት ሰራተኛዉ ለግዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን ባልደረባ ቶማስ ፍትህ ነግረውታል።
========//////////========
በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይዛ ከጅቡቲ ወደ የመን በማቅናት ላይ የነበረች ጀልባ ኤደን ባህረ ሰላጤ ውስጥ ሰጥማ የ38 ሰዎች ህይወት አለፈ።
አደጋው የደረሰው ከትናንት በስትያ መጋቢት 30/ 2016 ዓም ነው።
የተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ድርጅት በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች 64 እንደሚደርስ የጠቀሰ ሲሆን ህይወታቸው ሳያልፍ አይቀርም ያላቸው ተጨማሪ 6 ሰዎችም የገቡበት አልታወቀም ብሏል።
በአደጋው ህጻናትን ጨምሮ ለሞት ሲዳረጉ 22 ሰዎች ግን በህይወት ተገኝተዋል።
ስደተኞች በዚህ የጉዞ አቅጣጫ አደገኛ ሁኔታ እየገጠማቸው እንደሆነ ቢነገርም የስደተኞች ቁጥር አሁንም እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የፍልሰተኞች ተቋም አስታውቋል።