LOADING...

GTV

Trending Today
April 17, 2024

ዕለታዊ ዜናዎች ሚያዝያ 09/2016

By

በአማራ ክልል ህግ ማስከበር በሚል ሰበብ ወደ ክልሉ የገባው የአብይ አህመድ ጠባቂ ወታደር በሰፈረባቸዉ ካምፖች ንፁሀን ዜጎችን በመግደል በጀምላ መቅበሩን ከአገዛዙ የኮበለሉ የሰራዊቱ አባላት ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ተናገሩ።

ዛሬ ሚያዚያ 9/2016 ዓ/ም በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር መኮድ ካምፕ 8 ንፁሀን ዜጎች የፋኖ ቤተሰቦች ናቹህ በሚል ከተገደሉ በኋላ በጅምላ መቀበራቸውን ተከትሉ 18 የሰራዊቱ አባላት ከአገዛዙ ስርአት በመውጣት ፋኖን መቀላቀላቸውን ገልፀዋል።

ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድም ሰዉ ሳይገደል ውሎ አድሮ አያዉቅም ያሉት አባላቱ አገዛዙ ሲፈፅመዉ የቆየዉ የጅምላ ግድያ አማራን ከምድረገፅ ለማጥፋት እየተሰራ ያለ የፖለቲካ አሻጥር ነው ብለዋል።

በመኮድ ቅጥር ግቢ እና ከቅጥር ግቢው ዉጭ ብቻ ለቁጥር አስቸጋሪ የሆኑ የጀምላ መቃብሮች ሲኖሩ እኛ ያየነዉ ከ50 በላይ አለ ሲሉም ተናግረዋል።

በየቀኑ ከተለያዩ ቦታ ተጠርጥረዉ የሚመጡ ንፁሀን ዜጎች ከህግ ፊት ሳይቀርቡ ወደ ተቆፈረላቸዉ ጉድጓድ ይወሰዳሉም ብለዋል።

በብልጽግና ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ብዛት ያላቸዉ የጅምላ መቃብሮች እንዳሉ ሲነገር በድባንቄ ተራራ ብቻ ከ400 በላይ ንፁሃን በግፍ ግድያ መቀበራቸዉ ይነገራል።

ከዚህ በተጨማሪም በማዕከላዊ ጎንደር አዘዞ ካምፕ ከ30 በላይ የጅምላ መቀብር እንዳለም ቦታዉ ላይ የሚገኙ የግዮን ሳተላይት ቴሌቬዥን የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

መቃብሮቹ በአገዛዙ ወታደሮች እንደሚጠበቁ እንዲሁም ለጥበቃ የሚመደቡት የአንድ ብሄር ተወላጆች ብቻ መሆናቸዉንም ምንጮች ጠቅሰዋል።

በአንድ ምሽት ብቻ 60 ንፁሀን ዜጎች አዘዞ ላይ በግፍ ተገድለዋል፣ ቤተሰቦቻቸዉም አስካሁን ድረስ መሞታቸዉን አያውቁም የተባለ ሲሆን

ነገር ግን በዕስር ላይ እንደሚገኙ እና ወደ ሰባታሚት አንደሄዱ እንደሚናገሩ የውስጥ ምንጮችን አናግሮ ባልደረባችን ቶማስ ፍትህ ከስፍራው ዘግቧል።

========================//////////===========================

የብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ውስጥ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል እየፈፀመ ነው ተባለ::

አገዛዙ ሚስጥር ያወጣሉ በሚል ፍርሃት የአማራ ተወላጆችን ለይቶ እያሰረ እንደሆነም ነው የተነገረው::

የአብይ አህመድ አገዛዝ እየሄደበት ያለውን አደገኛ አካሄድ ቀድመው የተረዱና ፋኖን የተቀላቀሉ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለይም አማራ ሆነው አማራን እየወጉ ለሚገኙ የአገዛዙ ሰራዊቶች በጊዜ ነቅተው ከወጡበት ህዝብ ጎን እንዲቆሙ መልዕክት አስተላልፈዋል::

አገዛዙ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት እንደ መፍትሄ እየተጠቀመበት ይገኛል:: የሃገርን ዳር ድንበር ያስጠብቃል ተብሎ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መከልከያ ሰራዊትም የብልፅግና ተላላኪ ሆኖ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሰራ ነው:: ይህንን የብልፅግና ሴራ የተረዱ በመከላከያ ስር የነበሩ በርካታ የአማራ ተወላጆች ህዝባችንን አንወጋም በማለት ፋኖን ተቀላቅለዋል:: መከላከያን በመክዳት ፋኖን ከተቀላቀሉት መካከል የኦሮሞ ተወላጆችም ይገኙበታል:: የግዮን ቲቪ ሪፓርተር ቸርነት ተሰማ ከነዚህ ወታደሮች ጋር በነበረው ቆይታ የአማራ ተወላጅ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ በአዛዙ ሰዎች ሲደርስባቸው የነበረውን ግፍ እና ስቃይ ተናግረዋል::

የአገዛዙ ሰራዊት አማርኛ ሙዚቃ መስማት ሳይቀር አይፈቀድላቸውም:: ለከፍተኛ ግዳጅ ካልሆነ ሚስጥር እንዳያወጡ በሚል እንደሚታሰሩ በቅርቡ ፋኖን የተቀላቀለው የቀድሞው የአገዛዙ ሰራዊት ም/10 አለቃ አማረ ፈንቴ ለግዮን ቲቪ ተናግሯል:: ፋኖ የአማራ ጠላት ነው እናንተንም ካገኛችሁ አርዶ ይበላችሆል ስለዚህ ፋኖን ማጥፋት አለባችሁ የሚል ትእዛዝ ከአዛዙ እንደተሰጣቸውም እነዚህ ወታደሮች ተናግረዋል::

=======================///////////////////=======================

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ወረራ ፈፅሟል ሲል መግለጫ አውጥቷል።

የራሱን ህዝብ በመውጋት በማሳደድ እና በጅምላ በማስጨፍጨፍ የሚታወቀው የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ አማራውን አጋር ያደርግልኛል ያለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በባለፉት ሶስት ዙሮች በነበረው ውጊያ የፌዴራል መንግስቱን ጥረት ሲያወድስ የተስተዋለው መግለጫው
ህወሓት የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል ብሏል።

መላ የክልላችን ሕዝብ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ ሲል እያስገደለ ያለውን የአማራ ልጅ ወገኑን ለሌላ ፍጅት ጥሪውን አቅርቧል።

አጀንዳ እየተሰጠው ያለው ፋኖም ይህን ተጠባቂ መግለጫ ቀደም ብሎ መገመቱን ለማወቅ ተችሏል።

በህዝብ ስም ገንዘብ ለመለመን በጄኔቭ የተገኘው የአገዛዙ ልኡክ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አንቀፀስላሴም በተቃውሞው አትስደቡኝ ሲሉ ተሰምተዋል።

ትናንት በጄኔቭ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገንዘብ ለመለመን ተሰባስበው በነበረበት ወቅት ስብሰባው ፍፃሜ ላይ እጅግ በተጠና መንገድ ስብሰባውን ተቀላቅለው የነበሩ የአማራ ተወላጆች የፋኖ አባላት የአዳራሹን ትኩረት ስበዋል

አንድ የፋኖ አባል ታዬ አንቀፅስላሴን ሆድ አደር በማለት ያለበትን ሁኔታ መለስ ብሎ እንዲቃኝ ተናግሮታል።

አብይ አህመድ ገዳይ እንደሆነ በመግለፅም የአዳራሹን ትኩረት ስቧል።

ሌላኛው የአማራ ፋኖ በመነሳትም አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ የድሮን አረር እያዘነበ ነው እናንተ ለንፁሃን ግድያ ተባባሪ መሆን የለባችሁም የሚል መልእክት አስተላልፏል።

አማራ እየተጨፈጨፈ ነው አትተባበሩ በማለትም አሳስቧል።

ተቃዋሚዎቹ ታዬ አንቀፀስላሴን ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላይ ጭምር ከባድ ተቃውሞን አሰምተዋል።

በሁኔታው የተገረሙት የስብሰባው ተሳታፊዎች አጋጣሚውን በአንክሮ ሲከታተሉት የቆዩ ሲሆን ገሚሶቹም በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ምስል በማስቀረት ማስረጃ ሲሰበስቡ ታይተዋል ።

በተቃውሞው አምባሳደር ታዬ አንቀፀ ስላሴ በተረበሸ ስሜት እኔ እዚህ የመጣሁት ልሰደብ አይደለም በማለት ሲያማርሩ ታይተዋል።

ይህም ቢሆን ግን አገዛዙ በስብሰባው ላይ 154 ሚልየን ዶላር ለድርቅ ተጎጂዎች በሚል ቃል ተገብቶለታል።

ቃል ቢገባለትም ግን ከገጠመው ተቃውሞ አንፃር ይተገበራል ወይ የሚለው አጠያያቂ ሆኗል።
======///////=======

አገዛዙ የተራቆተውን ካዝናውን ለመሙላት አህመድ ሸዴንና ማሞ ምህረቱን ወደ ዋሽንግተን ልኳል።

እነዚህም ገና ስራቸውን ከመጀመራቸው ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

ይህና መሰል ሁኔታ የአገዛዙ ካድሬዎች እኩይ አላማቸውን እንዳያሳኩ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

የአማራ ክልል ተወካዮችም አሜሪካ ከገቡ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን ህዝብ እንዳያያቸው እንደ አይጥ በመሽሎክሎክ ላይ መሆናቸውን የግዮን ቴቪ ምንጮች አረጋግጠዋል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አገዛዙ ለመለመንና ገንዘብ ለመሰብሰብ እጅግ አዳጋች ሁኔታዎች ተጋርጠውበታል።
=======================////////////////===========================

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የሰሜን ወሎ ፀጥታ ኃይሎች ሚያዝያ 07/2016 ዓም በወልድያ ከተማ ዝግ ስብሰባ አካሂደዋል።

የክልሉ ፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሰሜን ወሎ ዞን ፀጥታ አመራሮችና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ መዋቅር እስከ ታችኛው ካቢኔ ዝግ ስብሰባ ማካሄዳቸውን ስብሰባውን የተሳተፉ አካላት ተናግረዋል።

የክልሉ ፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ አቶ ከበደ በወልድያ ከተማና በዙሪያዋ ያሉትን አድማ ብተና እና ሌሎች ሰላም አስከባሪዎችን ወደ ቆቦና ዋጃ እንደሚሰፍሩና የወልድያ ከተማን ጨምሮ በሌሎች ከተማዎች ያሉ ኬላ ጥበቃ ስራ እና ፀጥታ ማስከበር በፖሊስ ብቻ ይሸፈኑ የሚል ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል።

የሕወሓት ኃይሎች ከዋጃ እንዳያልፉ ከመከላከያና ከሕወሓት አመራሮች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን እና ምን አልባት ሊያልፉ እንኳን ቢችሉ እስከ ጥሙጋ ነው ከዛ በላይ አያልፉም ማለቱን የውስጥ ምንጮች ለግዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በዚህ መኃል ማንነቴንና እርስቴን አስመልሳለሁ የሚለው ፋኖ ከሕወሓት ኃይሎች ጋር ጦርነት ሊገጥም ይችላል። እኛ ፋኖን ከጀርባ ለመውጋት ዝግጁ መሆን አለብን ማለቱም ታውቋል።

ለዚህ ደግሞ በቅርቡ ተሀድሶ ተሰጥቶት የተመረቀው አድማ ብተናና ልዩ ኃይል ትልቁን ስራ ይሰራል።
በተጨማሪም መከላከያም ከባድ መሣሪያ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ቀጥታ ውጊያ እሰከማድረግ ይሳተፋል። እናንተም በዚህ ደረጃ ዝግጅታችሁን ቶሎ አጠናቅቁ የሚል የአለቆቹን ትእዛዝ ለተሳታፊዎች አስተላልፏል።

የክልሉ ፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ አቶ ከበደ የሕወሓት ኃይሎች አላማጣን እና ሌሎች ከተሞችን ስለያዙ ህዝቡ ተደናግጦ እና ተበሳጭቶ አሁን ከሚያደርገው በላይ ድጋፍ ለፋኖ እንዳያቀርብ እና በቀጥታም ወደ ፋኖ እንዳይቀላቀል እናንተ እንደ ዞን ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለባችሁ ሲልም ተደምጧል።

የሚያስቸግረው አካል ላይ ከባድ እርምጃ መውሰድ ግዴታችን ነው፣ በዚህ እርምጃችሁ ማሕበረሰቡ እንዲደናገጥና እንዲፈራ በማድረግ ከመንግስት ትዕዛዝ እንዳይወጣ አድርጉም ብሏል።

ህዝቡ ለመንግስት ለምን ለተደጋጋሚ ወረራ ዳረከን የሚል ጥያቄ ሊያነሳ ስለሚችልም እንደ መንግስት “መከላከያ ሰራዊቱ ፅንፈኞችን በማጥፋት ስራ ላይ ስለተጠመደ ሕወሓቶች ክፍተቱን ተጠቅመው ነው ያጠቋችሁ፣ ስለሆነም እናንተ ለፅንፈኛው ምሽግ ባትሆኑና ለማጥፋት ብትተባበሩ ባስቸኳይ ሕወሓትን ከአላማጣ የማስወጣት ስራ ይሰራ ነበር” የሚል ምላሽ ለመስጠት ታስቧል።እናንተም ይሄን ጥያቄ ለሚያነሳባችሁ የዞናችሁ ነዋሪ ይሄንኑ ምላሽ ስጡም ስለማለቱ ምንጮች ተናግረዋል።

በቤተክርስቲያን፣ በመስጂድ፣ በቅሬ፣ በሰንበቴ እና በእድር እንዲሁም ሌሎች ማሕበራዊ መገናኛዎችን ተጠቅማችሁ የሕወሓት ኃይሎችን ክፋት መዘርዘር እና ጥላሸት መቀባት አለባችሁ።

ምን አልባት ፋኖ ለሕወሓት ወረራ ምንም አይነት ምላሽ ባለመስጠት ከተባበረና በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ህዝቡን በየቀበሌው እየበሰባችሁ “ያ የምትመኩበት ፋኖ ስትወረሩ ምን አደረገላችሁ? እንደውም ከወራሪዎች ጋር በመተባበር እንድትወረሩ አድርጓችኋል” በሚል ሰፊ ቅስቀሳ በማድረግ ፋኖን ከህዝብ መነጠል ያስፈልጋል ሲል የክልሉ ፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ አቶ ከበደ መናገሩ ታውቋል።

የሕወሓት ኃይሎች ወደ አላማጣ እና ሌሎች ከተሞች መግባታቸውን ተከትሎም ግድያና ዘረፋ እንዲሁም መፈናቀል ሊኖር ይችላል። በተቻለ መጠን ይህ አጀንዳ ጎልቶ እንዳይወጣ የማፈን ስራ መሰራት አለበት በማለትም ለሰሜን ወሎ ጸጥታ ሃይሎች የዝግ ስብሰባ ትእዛዝ ተሰጥቷል ሲል ባልደረባችን መታፈሪያ ሃይሌ መረጃውን ከስፍራው ልኮልናል።

=========================///////////////////======================

የአገዛዙ ቁንጮ አብይ አህመድ የምእራባውያን አሻንጉሊት ወደ መሆን ደረጃ መሸጋገሩን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ለግዮን ቴቪ ተናገሩ።

እኚሁ ግለሰብ እንደገለፁት በቅርቡ አብይ አህመድ በርካታ ንግዶችን ለውጭ ባለሀብቶች መስጠቱ ከገጠመው የዶላር እጥረት የመነጨ ብቻ አይደለም ብለዋል።

በእርግጥ በአሁኑ ወቅት የአብይ አህመድ ካዝና የተራቆተ ነው በመሆኑም ሰውየው ዶላር ፍለጋ የሀገሪቷን ሀብት ለውጭ ባለሀብቶች አሳልፎ ቢሰጥ የሚገርም አይደለም ነገር ግን ምክንያቱ ዶላር ብቻ አይደለም ከዛ ይልቅ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ምእራባውያን አብይ አህመድን በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሱት እንደሚችሉ ማስፈራራታቸውን ቀጥለዋል፣ በደም የተነከረው አብይ አህመድም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የምእራባውያንን ፍላጎት እያሟላ ነው ባይ ናቸው።

እናም የውጭ ባለሀብቶችን በማስደሰት ስራ ላይ ተጠምዷል ያሉ ሲሆን ለወደፊትም አገዛዙ እስካለ ድረስ ለምእራባውያን ሰጥ ለጥ ብሎ እንደሚገዛም አልሸሸጉም።

የአብይ አህመድ አገዛዝ በቅርቡ የጫት የቡና ብሎም የቅመማ ቅመም ንግድን ለውጭ ባለሀብቶች አሳልፎ መስጠቱ አይዘነጋም።

እንደ አስተያየት ሰጭው እምነት አብይ አህመድ የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ከአለም አቀፍ የጦር ወንጀለኛነት ለማምለጥም ጭምር ነው።

Prev Post

ዕለታዊ ዜናዎች

Next Post

Amhara Fano Liberated Jawi &…

post-bars

Leave a Comment