ዕለታዊ ዜናዎች
በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የከሰም ክፍለ ጦር ተስፋ ብርጌድ ፣ የነበልባል ብርጌድ እና ኃይለማርያም ማሞ ብርጌዶች ባካሄዱት ውጊያ ከፍተኛ ድል ተመዘገበ።
በአርበኛ እና ደራሲ አሰግድ መኮንን የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ብርጌድ ሚያዝያ 9 ሌሊቱን ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በ ፶/አለቃ ጎሽመው ኃይሌ የሚመራው በበረኸት ወረዳ የሚንቀሳቀሰው ተስፋ ብርጌድ ሚያዝያ 9 ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ለተከታታይ 8 ሰዓታት ራሱን ጥምር ጦር ብሎ ከሚጠራው የአገዛዙ ጠባቂ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ የአገዛዙን ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ያደረገ ሲሆን ምርኮዎችንም አግኝቷል።
በዕለቱ ጦርነት በተደረገባቸው ቀበሌ 09፣ ቀበሌ 02፣ ዋንሴ፣ ፍርዱ ሃገር፣ ደመወዜ፣ አቤቶ እና መሃል በረኸት ላይ ወራሪው ሃይል ተደምስሶ 3000 (ሶስት ሽህ) የክላሽ ጥይት፣ 50 የጀርባ ቦርሳ እና በርካታ ክላሽንኮቭ መሳሪያዎች በበረኸቶቹ የበረሃ ነብሮች ምርኮ አድራጊነት ወደ ተስፋ ብርጌድ ገቢ ተደርጓል።
በምንጃር አረርቲ ከተማ የስርዓቱ ጠባቂ ጥምር ሃይል በካምፕነት በሚገለገልበት የምንጃር ሸንኮራ የወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይም ሚያዝያ 9 አዳሩን የነበልባል ብርጌድ እርምጃ ወስዷል።
የምንጃር ሸንኮራ የነበልባል ብርጌድ ፉኖዎች ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ
በከተማዋ ሰርጎ በመግባት በወራሪው ራሱን መከላከያ ብሎ በሚጠራው ዙፋን አስጠባቂ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ፣ የአማራ አድማ ብተና እና የአማራ ሚሊሻ ላይ እርምጃ ወስዷል።
በተለይም ራሱን ጥምር ጦር ብሎ በሚጠራው የአገዛዙ ሃይል ላይ ድገተኛ ጥቃት በማድረስም በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።
በዚህ ኦፕሬሽን በፋኖ ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስም ከአረርቲ ከተማ ለቆ መውጣት ተችሏል።
በተያያዘም በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለ ጦር በነበልባል ብርጌድ በሸንኮራ ንኡስ ወረዳ በባልጪ ከተማ የአገዛዙ ሃይል በካምፕነት የሚጠቀምበት ፖሊስ ጣቢያ ሚያዝያ 9 ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ ፋኖ ሰርጎ በመግባት ራሱን ጥምር ጦር ብሎ በሚጠራው ሃይል ላይ እርምጃ ወስዷል።
የአገዛዙን ሰራዊት በመግደል እና በማቁሰልም የነበልባል ብርጌድ ባቀደው መሰረት ኦፕሬሽኑን ሰርቶ ምንም ጉዳት ሳያስተናግድ የባልጪ ከተማን ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ ለቆ ወጥቷል።
ሚያዝያ 9 አዳሩን ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው ወራሪ ሃይልም በደረሰበት ጉዳት በእጅጉ በመበሳጨቱ የበቀል በትሩን ሚያዝያ 10 ቀኑን ሙሉ በምንጃር አረርቲ ከተማ በሚኖሩ ንፁሃን አማራዎች፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን እና የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ድብደባ እና እስር ሲፈጽም ውሏል።
በተያያዘ ዜና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የከሰም ክፍለ ጦር የሃይለማርያም ማሞ ብርጌድ በሃገረ ማርያም ከሰም ወረዳ በሾላ ገበያ ከተማ ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ወደ ከተማዋ በመግባት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
ፋኖዎቹ የአገዛዙ ጥምር ጦር በሰፈረበት ቦታ በመጠጋት በተለምዶ ካንቦ ማርያም በሚባል አካባቢ እና አስተዳደር ግቢ በመግባት ጥቃት በማድረስ የስርዓቱን አስጠባቂ ሃይል ሙት እና ቁስለኛ አድርገው ተልእኳቸውን አሳክተው ያለምንም ጉዳት ከተማዋን ለቀው ወተዋል።
የከሰም ክፍለ ጦር በስሩ ካሉት አራት ብርጌዶች ውስጥ ሶስቱን አናቦ ስራ በመስራቱም የተሻለ ውጤት እንዲገኝ አድርጓል።
በተስፋ መቁረጥ እና በውድቀት ዋዜማ ላይ የሚገኘው የስርአቱ ጠባቂ ሰራዊትም ፋኖን የመቀላቀል ፍላጎቱ እየጨመረ መሄዱም ተነግሯል።
ዘገባዎቹን የጊዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን ዘጋቢያችን በቃሉ ደረሰ ከሸዋ ልኮልናል።
========///////=========
የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ፅፈት ቤት አዛዥ መገደሉ ተነገረ።
የዞኑ ፖሊስ ፅ/ቤት ዋና አዛዥ ኮማንደር የማተዉ ምህረቴ ዛሬ ሚያዚያ 10/2016 ዓ/ም ከጧቱ 2:00 በዞኑ መናገሻ ዋና ከተማ ደብረ ታቦር ቴክኒክ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መኖርያ ቤቱ እርምጃ ተወስዶበታል።
እርምጃውን ተከትሎ የአገዛዙ ሰራዊት በወሰደው አጸፋ በጉዳዩ ያልተሳተፉ ሁለት ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል።
ኮማንደር የማተዉ ምህረቴ ከዚህ በፊት የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ የነበረ ሲሆን በፋርጣ ወረዳ ጋሳኝ ከተማ 26 ወጣቶችን ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ወታደር ጋር በመሆን በጀምላ ያስጨፈጨፈ ብዙሀኖችን ደግሞ የአካል ጉዳተኛ እንዲሆኑ ያስደረገ ግለሰብ ነበር።
በዚህ አስከፊ ስራዉ የሚታወቀው ኮማንደሩ በብልፅግናው አስተዳደር ታታሪ ሰራተኛ በመባል የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥም ተደርጓል።
በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ፣እብናት፣መና መቀጠዋ፣ጎና በጌምድር ፣ታች ጋይንት እንዲሁም አንዳ ቤት ወረዳ ከ78 በላይ አርሶ አደሮች እንዲገደሉ ሲያደርግ በደብረታቦር ከተማ ወጣቶች በጅምላ እንዲገደሉ እና እንዲታሰሩ ሲያደረግም ቆይቷል።
እርምጃዉን የወሰደዉ የአማራ ፋኖ በጎንደር የጉና ክፍለጦር እንደሆነም ተገልጿል።
========///////=========
የዲያስፖራው ሚዲያዎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር እየሰሩ አስቸግረውናል ሲል የአገዛዙ ቁንጮ አማካሪ ዳንኤል ክብረት አማረረ።
እንደዲያቆኑ ገለፃ አሁን ደግሞ በቴሌቪዥን ጭምርም መጥተውብናል ሲል ስጋቱን ገልጿል
የአገዛዙ ቁንጮ የእነ ግብፅ ተላላኪ ብሎም ኦነግ ስለመሆኑ በአደባባይ ሲናገር መስማት የተለመደ ሆኖ ቆይቷል
ይህንንም የሚያደርገው የገዛ ፓርቲውን ኢህአዴግን ለመጣል እንደነበርም በራሱ አንደበት ይመሰክራል
ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዱሉ ራሱ ብልጽግና ውስጥ ያሉ ሰዎችም ሳይቀሩ ፓርቲውን ለመጣል እየተረባረቡ ይገኛሉ በሌላ በኩልም በውጭ ሀገር የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎችን በመክፈት ሀገሪቷን ለማዳን በመስራት ላይ ናቸው በዚህ የተበሳጩት የአገዛዙ ቁንጮ አማካሪ ዳንኤል ክብረት ዲያስፖራው ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመተባበር በሚዲያ ዘምቶብናል ሲሉ አማረዋል::
አብዛዎቹ በውጭ ሀገር ዲያስፖራዎች የሚሰሩ ሚዲያዎችም ባለቤትነታቸው የውጭ ሀገር መንግስታት ናቸው በማለትም ወቅሰዋል ዳንኤል ክብረት ይህን ቢሉም ግን ለዚህ ክሳቸው አንድም ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም የዳንኤል ክብረትን ክስ በተመለከተ አስተያየቱን የሰጠው አንድ አንጋፋ ጋዜጠኛ ክሱን አስቂኝ ነው ብሎታል
በአለም ጋዜጠኞችን በማሰር በመግረፍ ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረግና በአጠቃላይ የሀገሪቱን እስር ቤቶች በጋዜጠኞች የሞላ መንግስት ይህን ማለቱ ግራ መጋባቱን ያመላክታል ብሏል
በዚህ መንገድ ህዝብ እንደ ህዝብ የታፈነባት ኢትዮጵያ ላይ ለምን ድምፅ ሆናችሁ ብሎ መክሰስ አፋኝ መንግስት እንደሆነ አረጋጋጭ ነውም ብሏል
የአለም አቀፉ የጋዜጦች ተሟጋች ተቋም CPJ በተደጋጋሚ በሚያወጣው ሪፖርት አገዛዙ ጋዜጠኞችን በማሰር ረገድ ከአለም ቁጥር አንድ ደረጃ ላይ ደርሷል በማለት ይከሳል ሌሎች በርካታ ተቋማትም ኢትዮጵያ ለጋዜጠኞች አስፈሪ ሀገር ናት በማለት ክሳቸውን በመዘርዘር ላይ ናቸው ይህን ሁሉ እውነታ ወደ ጎን በመተው ዲያቆን ዳንኤል ክስ ይዘው መቅረባቸውንና ብዙዎቹን አነጋግሯል
========///////=========
የአገዛዙ ፍርድ ቤት ቄሲስ በላይ መኮንን በእስር እንዲቆይ ፈቀደ።
ቄሲስ በላይ ከሁለት ቀናት በፊት በአፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ ስድስት ሚልዮን ሀምሳ ሺህ ዶላር ለማስተላለፍ ሲሞክር እጅ ከፍንጅ መያዙ አይዘነጋም።
በዚህ መጠን ይህ ሁሉ ገንዘብ ሊዘረፍ መታሰቡ በበርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል ።
ሰውየው ከአገዛዙ ዘራፊ ባለስልጣናት ጋር በቅርበት አብሮ እየሰራ እንደነበረም የግዮን የውስጥ ምንጮች አረጋግጠዋል።
ሰውየው ፍርድ ቤት ሲቀርብም ድርጊቱን መፈፀሙን ገልፆ ጥፋተኛ ግን አይደለሁም ሲል ተናግሯል።
ቀሲስ በላይ ይህን ሁሉ ገንዘብ ለማስተላለፍ ሲሞክር በሁኔታው የተደናገጡት የባንኩ ሰራተኞች ለፖሊስ ደውለው በቁጥጥር ስር ውሏል ።
በወቅቱ ፖሊስ ሲይዘው ቆይ አንድ ግዜ ለአብይ አህመድ ስልክ ልደውል ማለቱ ዘረፋውን የአገዛዙ ቁንጮ ጭምር የሚያውቁት ስለመሆኑ አመላካች ነውም ተብሏል።
እስካሁን ድረስ ይህ ሁሉ ገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ ለማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ሀገሪቱ ግን በዘርፋ ኔትወርክ እየተመዘበረች ስለመሆኑ አመላካች ነው።
ራሳቸውን በአገዛዙ ሸፍነው ዘረፋ የሚፈፅሙ ሰዎችም ተበራክተዋል ተብሏል።
========///////========
ለሰብአዊ ቀውስ ድጋፍ አንድ ቢሊዮን ዶላር የጠየቀችው ኢትዮጵያ 610 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ከሃገራት ቃል አግኝታለች።
በጄኔቫ በተደረገው አለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ የእርዱኝ ጥያቄ ያቀረበችው ኢትዮጵያ ይህንን ድጋፍ በአንድ ጊዜ ሳይሆን አመታትን ሊፈጅ በሚችል ሂደት እንደምታገኘው ነው የተነገረው።
ከ20 ሃገራት ውስጥ 154 ሚሊዮን ዶላሩን አሜሪካ ስለመስጠቷም ታውቋል።
ከዚህ ቀደም ያሉ ልምዶች እንደሚያሳዩት መሰል ድጋፍ በሃገራት የሚፈጸመው ባልተሟላ የክፍያ ስርአት ነው።
ከ15 ሚሊዮኖን በላይ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በርሃብ እና በጦርነት እያለቁባት ያለችው ሃገሪቱ በመንግስት በተጠነሰሰ እልቂት አሁንም ችግሩን እያባባሰች ቀጥላለች።
ሃገራቱ ይህንን ድጋፍ ያደረጉት በሃገሪቱ እየከፋ በሄደው ጦርነት መፈናቀል እና ርሃብ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የስደት ጎርፍ ከወዲሁ ለመከላከል እንዲያስችላቸው መሆኑን አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።