LOADING...

GTV

Trending Today
April 19, 2024

ዕለታዊ ዜናዎች ሚያዝያ 11/2016ዓ.ም

By

መላው የአማራ ህዝብ ዛሬም እንደ ትናንቱ የውስጥ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ወራሪውን ሕወሐት በጋራ እንዲፋለም የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚቴው ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ወልቃይትን በሕወሐት መልሶ ማስደፈር የሚቻለው በመቃብራችን ላይ ብቻ ነው ብሏል።
ይህን መፍቀድ ራስን በራስ እንደማጥፋት ይቆጠራል ሲልም መግለጫው አትቷል።
ሕወሐት ታጣቂዎቹን አሰልፎ ታጥቆ እየመጣብህ ነው ያለው መግለጫው የወልቃይትና የጠቅዴ ሕዝብ የራሱን ነጻነት እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።
የብልጽግናው አገዛዝ ሽንፈት እየገጠመው ሲመጣ የትግራይና የአማራ ሕዝብን እንደገና ለማገዳደል እየሰራ ሰለሆነ ጥንቃቀ እንደሚያስፈልግ ፈኖ ሲያስጠነቀቀ መሰንበቱ ይታወሳል።
አድማጭ ተመልካቾቻን የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሙሉ መግለጫን ከዜና በኋላ እናቀረባለን።
=================//================
የአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊት የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ተጠምዷል ሲል ቢቢሲ ባካሄደው
የምረመራ ዘገባ አጋለጠ።
ቢቢሲ ባቀረበው የምርመራ ዘገባ እንዳለው የአገዛዙ ቁንጮ የህዝብ ድጋፍ እንዳለው ለማስመሰል የሚዲያ ሰራዊቱ እየተፍጨረጨረ ነው።
ቢቢሲ ይህንን ምርመራ ዘገባ ለመስራት ሶስት ወራት ፈጅቶበታል።

የአገዛዙ ቁንጮ ዐብይ አህመድ ህዝብን ለማደናገር ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ ማህበራዊ ሚዲያ ነው ።
በግሉ ሳይቀር የምለጥፈውን መረጃ ውደዱልኝ አጋሩልኝ በማለት እንደሚታወቅም ከቤተመንግስት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
አሁን ደግሞ በዚህ ረገድ አገዛዙን የሚያጋልጥ የምርመራ ዘገባ በቢቢሲ በኩል ወጥቷል።
የምርመራ ዘገባው እንዳረጋገጠው የአገዛዙ ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት ዐብይ አህመድ የህዝብ ድጋፍ እንዳለው ለማስመሰል አጥብቆ እየሰራ ነው። አብይ አህመድን የሚቃወሙ አካላትን ደግሞ ያሳድዳል።
ሀሰተኛ በሆነ መንገድ የአገዛዙን ጠቅላይ ሚንስትር ገፅታ ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች የተጠኑና የተቀናጁ እንደሆኑም ቢቢሲ አረጋግጧል ።በዚህ ዘመቻም የአዲስ አበባ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ጭምር ተሳታፊ እንደሆኑ ነው የገለጸው።
ይህ ሰራዊት ስለ አገዛዙ ያለው ሀቅ እንዳይወጣ የሀሰት መረጃ በመስጠት እንደሚረባረብም በዘገባው ተመልክቷል።
ይህ ብቻ አይደለም የአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊት የሀሰት ዜናዎችን በመቀባበል ህዝቡን እንደሚያደናግር ተረጋግጧል ።
ለዚህም በማሳያነት የቀረበው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ሲወጡ አይመለሱም የሚል የሀሰት መረጃ ሆን ተብሎ መሰራጨቱ ነው ይላል።
የጳጳሱ የሀሰት ዜና አንድ ሺህ አራት ጊዜ እንዲለጠፍ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ ዐብይ አህመድን ባጋለጠበት ፅሁፍ ላይ ሰራዊቱ ተከታታይ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲያሰራጭ ተደርጓል።
ይህም ትእዛዝ የመጣው ከአገዛዙ ቁንጮ ዐብይ አህመድ መሆኑን ይሄው ምርመራ አረጋግጧል።
የአብይ አህመድ የሚዲያ ሰራዊት በዚህ ብቻ ሳይገደብ በህወሓት አመራሮች ላይ ጭምር እንደሚዘምትም ተመልክቷል። አገዛዙን በመቃወም ፅሁፍ የሚለጥፉ ሰዎች ላይምየጥላቻ ንግግር በማድረግ ለማሸማቀቅ እንደሚሞከርም ነው የተገለጸው።
ለዚህ የሚዲያ ሰራዊት ቡድንም ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚከፈል ታውቋል።
የአገዛዙ ቁንጮ አማካሪ ዳንኤል ክብረት ትላንት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ አፍራሽ አስተያየት ከሰጠ በኋላ ይህ ሪፖርት መውጣቱ ጉዳዩን የበለጠ አነጋጋሪ አድርጎታል።

የአገዛዙን ገመና በቢቢሲ ሲጋለጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ከሶስት ወራት በፊትም ሮይተርስ ለስድስት ወራት በሰራው ምርመራ አገዛዙ ኮሬ ነጌኛ የተባለ ገዳይ ቡድን ማደራጀቱን እንዳጋለጠ አይዘነጋም ይህ ገዳይ ቡድን የአገዛዙ ቁንጮ ስጋት ናቸው የተባሉ ግለሰቦችን የማስወገድ ስራ ተሰቶታል

አገዛዙ እስካሁን ድረስ በተጋለጠበት ጉዳይ ላይ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል

=================//================
በሰሜን ወሎ ዋድላ ወረዳ ውስጥ ከ150 በላይ የሚሊሻ አባላት እርምጃ ተወሰደባቸው።
በዋድላ ወረዳ ቋና ቀበሌ ከ150 በላይ የሚሆኑ የሚሊሻ አባላት ግዳጅ ላይ ተጠርንፈው እንደተቀመጡ በፋኖ በተወሰደባቸው እርምጃ 12ቱ ሲገደሉ ከ30 በላይ ቆስለዋል።
ከ150 በላይ በሚሆኑ ሚሊሻዎች ላይ ሚያዝያ 10/2016 ዓ/ም አዳሩን በፋኖ በተወሰደ ጥቃት 12ቱ ሲገደሉ ከ30 በላይ መቁሰላቸውንና 12ቱም መማረካቸው ተገልጿል።
አዳሩን በዋድላ ወረዳ ቋና ቀበሌ በነበረ የሚሊሻ ካምፕ ላይ እርምጃውን የወሰዱት በወሎ ዕዝ ላስታ አሳምነው ፅጌ ክፍለ ጦር የፅናት ሻለቃ ፋኖዎች መሆናቸው ታውቋል።
የወሎ ፋኖዎች በፈጸሙት በዚሁ ኦፕሬሽን ቋና ቀበሌ የነበረው የአገዛዙ ሚሊሺያዎች ካምፕ ተይዟል።
ብጥቃቱ የቆሰሉት የሚሊሻ አባላት ኮን ከተማ ወደ ሚገኘው የወረዳው መለስተኛ ሆስፒታል ለህክምና መላካቸውን የዕዙ ህዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
=================//================
የሰሜን ወሎ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የአገዛዙ አመራሮች ለምስራቅ አማራ ፋኖ የእንደራደር ተማፅኖ ማቅረባቸው ተሰማ።
በተለይም በአገዛዙ ፊቃድ ህውሐት የፕሪቶሪያ ስምምነቱን በመጣስ በራያ አካባቢ የአማራ ግዛቶች ላይ ለአራተኛ ጊዜ የፈፀመው ወራራ የሰሜን ወሎን የአገዛዙ ሃላፊዎች ውጥረት ውስጥ ከቷቸዋል ተብሏል።
የምስራቅ አማራ ፋኖ ግን የድረድር ጥያቄውን እንደማይቀበል አስታውቋል::

የአማራን ህዝብ የአመታት ሰላማዊ ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ህዝቡን ሲጨፈጭፍ የነበረው የብልፅግና አገዛዝ በመጨረሻው ሰአት የደረሰበትን ሽንፈት አምኖ ስለመቀበሉ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ነው የተገለፀው::

እያገለገሉት በሚገኙት የብልፅግና ፓርቲ ላይም እምነት እጥተዋል:: ምክንያቱ ደግሞ እነዚህን አመራሮች ከውጡበት ህዝብ ጎን ቆመው እንዳይታገሉ በጥቅማ ጥቅም ከህዝባቸው ጋር መቃቃር ውስጥ ካስገባቸው በሗላ ለህውሃት ወራሪ ሃይል አሳልፎ ሰጥቷቸዋል:: በቅርቡ ከህውሃት ወረራ ሲሸሽ በመከላከያ የተገደለው የራያ አላማጣ እስተዳዳሪ ግድያ አገዛዙን አምነው ለሚያገለግሉት እንኳን ቅንጣት ያህል ርህራሄ እንደሌለው የሚያሳይ ነው:: አገዛዙ የአላማጣ አስተዳዳሪ ግድያ ማንም እንዳይሰማው በሚል አፍኖ መያዙንም ከውስጥ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

አንድ አመት ሊያስቆጥር የተቃረበው የፋኖ ትግል እስከ ትግሉ ፍፃሜ እንደሚቀጥል እና የብልፅግና ከንቱ ፉከራም ሆነ ተማፅኖ ትግሉን ለደቂቃ ወደህላ እደማያስቀረው የምስራቅ አማራ ፋኖ መልዕክት አስተላልፈዋል:: የብልፅግና የእንደራደር ጥያቄም ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ በሁሉም አቅጣጫ የሚገኝ ፋኖ እንደዚህ አይነት ተራ ጥያቄዎችን ወደ ጎን በመተው የተሰው የትግል ጏዶችን አደራ ለመፈጸም እስከመጨረሻው እንደሚታገሉ ገልፀዋል::

በሌላ በኩል ህውሃት የአማራን ግዛቶች በእገዛዙ ድጋፍ ስጭነት በሃይል ለመውረር ቢሞክርም በነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለፀ::

በህውሃት ተደጋጋሚ የወረራ ጥቃት የተማረሩት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የአላማጣ ከተማና ዙሪያ የሚገኙ ቀበሌዎች ህውሃት ይውጣልን እኛ አማራዎች ነንየሚል ተቃውሞ እያሰሙ እንደሆነ ተገልጿል::

የህወሃት ታጣቂዎች በእነዚህ የአማራ ግዛቶች በ10 ሺህ የሚቆጠሩ በሬ፣ላም፣ ፍየል በግ፣አሃያና ግመል ነድተው እንደወሰዱ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ በተጨማሪ በየሰው ቤት በመግባት እህል፣ ወርቅ፣ስልክ፣ገንዘብ የገበሬ እርሻ በቆሎ እና ቲማቲም የበሉትን በልተው ቀሪውን አውድመውት ሄደዋልም ብለዋል።

በዚህም ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች መኖርያ ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነም ነው የተነገረው::

=================//================
በደቡብ ጎንደር ደራ ፥ ሀሙሲት፥ አርብ ገብያ እና ገላዉዲወስ ከተሞች ከአገዛዙ ሰራዊትት ነፃ መውጣታቸው ተነገረ።
ላለፉት 9 ወራቶች ከፍተኛ ተጋድሎ ሲደረግባቸዉ የቆዩት እነዚህ ከተሞች ከፀረ አማራዉ የአገዛዝ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸዉን የጀኔራል ነጋ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ገልጸዋል።
ባለፉት ሶስት ቀናት በቀጠናው የጉና ክፍሐጦር እና የጀኔራል ነጋ ክፍለጦር በጋራ ባካሄዱት ዘመቻ የደራ ሀሙሲት አርብ ጣብያ ከተማ እና ገላዉዲወስ እንዲሁም ማህደረ ማርያም እና ልጫ ከተሞች ከአገዛዙ ነፃ ወጥተዋል።
በዚሁ ዘመቻ ከ45 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ በተሰዋበት አካባቢ ሲደመሰስ ከ70 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ፋኖን ተቀላቅለዋል።
በዚህ አዉደዉጊያ ከ1 መቶ በላይ የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሳሪያ እና ከ8 በላይ የቡድን መሳሪያ ተማርኳል።
አገዛዙ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ የሎጀስቲክ አቅርቦቶችም ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙ ተደርጓል።
በቀጠናዉ ከባድ አዉደ ዉጊያ ሲደረግ ከቆየ በኋላ የአፄዋቹ ልጆች ሚያዚያ 11/2016 ዓ/ም ከአምስት በላይ ከተሞችን ከአገዛዙ ሀይል በመንጠቅ ነፃ ማዉጣት ችለዋል።
በዚሁ ቀጠና የአድማ ብተናና የሚሊሻ አባላት በነበረዉ አዉደዉጊያ ከእዉነት አልተዋጋችሁም በሚል 3 የአድማ ብተናና 2 የሚሊሻ አባላት በአገዛዙ ሰራዉት ተረሽነዋል።
ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መታሰራቸዉን የዉስጥ ምንጮቻችን ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎ በአገዛዙ ታጣቂዎች መካከል የዕርስ በዕርስ ግጭቱ ተጠናክሮ በመቀጠሉ በዚሁ ዕለት ብቻ 30 የሚደርሱ አድማ ብተናና ሚሊሻ ፋኖን ተቀላቅለዋል::
=================//================
በአገዛዙ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የሚመራው የባህር ዳር አስተዳደር በከተማዋ ያሉ ነጋዴዎችን ግብር ክፈሉ በማለት እያስጨነቃቸው መሆኑ ተሰማ።
ግብር አንከፍልም ያሉ የተለያዩ ግለሰቦች በከተማዋ አስተዳደር ወከባ እየደረሰባቸው ሲሆን ድርጅታቸውም ያለፍርድ ቤት ትዛዝ እየታሸገባቸው ይገኛል።
በዚህም የተነሳ ጉዳዩን በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዩት የግዮናውያን ተከላካይ ንሥሮች በዳግማዊ ምንይልክ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሐያት ፔንሲዮን አከባቢ የተለያዩ ሱቆችንና ድርጅቶችን ሲያሽጉ በተገኙ ሶስት የአገዛዙ ጉዳይ ፈፃሚዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ፈጽመውባቸዋል።
ከዚህ በኋላም የአማራን ህዝብ በማስጨነቅ ባሉ መሰል ተላላኪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ሲሉ ንስሮቹ አሳስበዋል።
የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ከትግራይ ጋር በተካሄደው ጦርነት ጊዜ ሕወሐት መጣ በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከብአዴን ካዝና በብድር ስም ዘርፎ ከተባረሩት ባለስልጣናት አንዱ ነበር።
አሁን ግን በአረጋ ከበደ የምስለኔ አስተዳድር እንደገኛ ተሹሞ የባህርዳርን ሕዝብ እያሰቃየ ይገኛል::

Prev Post

ዕለታዊ ዜናዎች

Next Post

BBC Amharic Exposed Abiy Ahmed’s…

post-bars

Leave a Comment