የፋኖ አንድ ጠቅላይ እዝ ለመመስረት እንቅስቃሴ መጀመር – ሚያዝያ 14/2016 ዕለታዊ ዜናዎች
ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገውምድር ክፍለ ጦር የወርቅ አባይ ብርጌድ ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል።
በአዊ ዞን በዚገም ወረዳ በተደረገ ውጊያ የወርቅ አባይ ብርጌድ አስደማሚ ጀብዱ መፈፀሙን ከዋና አዛዥ ከሻለቃ በላይ ዘለቀ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
በዚህም 53 የአገዛዙ ኃይል አባላት ተገለዋል:: ከእነዚህም ውስጥ 5 ከፍተኛ የፖሊስና አድማብተና አዛዦች እንደሚገኙበት ከማዕረግ መለዮቸው ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህም በተጨማሪ 173 የፋሽስቱ ኃይሎች ቆስለዋል:: በዚህ ወቅትም ቻግኒና እንጅባራ ሆስፒታሎች እንዲሁም ቲሊሊ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ እንዳሉ ታውቋል።
ሌሎች 28 የአድማብተና አባላት ደግሞ በዚሁ የውጊያ ቀጠና እጃቸውን መስጠታቸው ተገልጿል::
1 ብሬንን ጨምሮ በርካታ ክላሽንኮቭና ተተኳሾችም መማረካቸውም ታውቋል ሲል ዘገባውን ከስፍራው ያደረሰን መታፈሪያ ሃይሌ ነው::
========////////=========
የፋኖ አዛዦች ወደ አንድ ጠቅላይ እዝ የመምጣት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን በይፋ አስታወቁ::
የአማራ ፋኖ ወደ አንድ ማዕከላዊ መምሪያ እየመጣ መሆኑን በሁሉም ግዛቶች ያሉ የፋኖ አዛዦች በአጽንኦት በመግለፅ ላይ ናቸው::
የወሎ እዝ አዛዡ ኮለኔል ፈንታው ሙሃቤ ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ ፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ እዝ አዛዥ ሻለቃ መከታው ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናው ከሰሞኑ አንድ የአማራ ፋኖ እዝ ለመመስረት እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ “በጎበዝ አላቃ የነበረውን የፋኖ አደረጃጀት “ ከሻለቃ ወደ ብርጌድ ፣ ከብርጌድ ወደ ክፍለጦር ፣ ከክፍለጦር ወደ እዝ አሳድገናል” ብሏል፡፡
አሁን ላይ ፋኖ የተሻለ አቅም ላይ ይገኛል ያለው የፋኖ አዛዡ በየአቅጣጫው ያለው የብልጽግና ጦር ብትንትኑ እየወጣ ነው ሲል ገልጿል፡፡
አክሎም ሁሉም የአማራ ፋኖ በጋራ አንድ ቤት ለመስራት ጥረት እያደረገ እና በጉዳዮም ላይ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ አስታውቋል::
አያይዞም ህወሃት የአማራ ግዛቶችን መውረሩን በሚመለከት በሰጠው አስተያየት “አማራ በሁሉም አቅጣጫ ተከቦ ባለበት ወቅት ወጣቱ ወደ ትግል ከመግባት ውጪ አማራጭ የለውም ብሏል፡፡
========//////////=======
በአዲስ አበባ የሚገኙ ሰባት ኤምባሲዎች የሰሞኑ የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ ስጋት ውስጥ ከቶናል በማለት የጋራ አጭር መግለጫ አወጡ::
መግለጫውን ያወጡት
የካናዳ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የጣሊያን፣ የጃፓን፣ የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች በጋራ በመሆን ነው::
በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ “አወዛጋቢ ” በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት ” ስጋት ፈጥሮብናል ” ብለዋል።
የሁሉም ወገኖች ታጣቂ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት እንዲሁም ተፈናቃዮችን በሰላም ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ መሰራት አለበት ሲሉ ገልፀዋል::
” ውጥረቱ እንዲረግብ እና ሰላማዊ_ሰዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸውም እናሳስባለን ” ብለዋል በመግለጫው::
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የተወሳሰቡ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም ጨምረው ገልፀዋል::
=========/////////=======
አገዛዙ ከውጭ ገንዘብ ለመለመን ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን የፈረንሳይ ሬዲዮ ዘገበ
በሌላ በኩል የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ከአገዛዙ ባለስልጣናት ጋር እንደማይነጋገሩ ታውቋል::
ባለፈው ሚያዝያ ስምንት በጄኔቭ በተካሄደ ስብሰባ አገዛዙ 3.2 ቢልየን ዶላር ጠብቆ ነበር
ሆኖም ስብሰባው እንደተጠበቀው አልሆነም የአማራ ተቃዋሚዎች ለጋሾች የሚሰጡት ገንዘብ ለድሮን መግዣ የሚውል ነው በማለት ተቃውመዋል የአገዛዙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርንም አዋርደዋል
አገዛዙ በበኩሉ 21 ሚልዮን ህዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ይፈልጋል በማለት ልመናውን ቀጥሎ ነበር የአማራ ተቃዋሚዎች የፈፀሙት ተግባር በሶሻል ሚዲያ ተወዳጅነትን ለማግኘት ነው በሚል መቀለዱም አይዘነጋም ሆኖም ነገሩ ወዲህ ነው
የፈረንሳይ ሬዲዮ እንደዘገበው ለጋሾች ለአገዛዙ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት የላቸውም በስብሰባው ላይ ቃል የተገባው 600 ሚልየን ዶላር ሲሆን ከዛም ውስጥ 300 ሚልዮን ዶላር እራሱ አገዛዙ እሰጣለሁ ያለው የገንዘብ መጠን ነው በመሆኑም ቃል የተገባለት ገንዘብ ከ 300 ሚልየን ዶላር አይበልጥም በመሆኑም አገዛዙ ገንዘብ ለመለመን ሁለተኛ ዙር ስብሰባ መጥራቱን ሬዲዮ ጣቢያው አረጋግጧል
ለዚህ የአገዛዙ እቅድ ኪሳራ ምክንያቱ የአማራ ተቃዋሚዎች በአዳራሹ ላይ ያስተላለፉት መልእክት እንደሆነ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ምሁር ለጊዮን ቴሌቪዥን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል እንደ ምጣኔ ሀብት ምሁሩ ገለፃ በተለይ በአማራ ተቃዋሚዎች የሚደረገው እንቅስቃሴ በአገዛዙ ላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫና ሊፈጥር ይችላል እናም በሂደት አገዛዙ እጅ ወደ መስጠት ሊሸጋገር ይችላል ባይ ናቸው ለዚህም ምክንያት ብለው የሚያቀርቡት አገዛዙ ከውስጥም ከውጭም አካላት እየተነጠለ መምጣቱ ነው
አስተያየት ሰጭው ጨምረው እንደገለፁት በቅርቡ እንኳን የአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ለአገዛዙ ሰዎች ያሳዩት ምላሽ ችግሮች ስር እየሰደዱ ስለመምጣታቸው አንዱ ማሳያ ነው በሌላ በኩል የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል ምክትል ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡም ከአገዛዙ ሰዎች ጋር ለመነጋገር ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል ይህም በአገዛዙ ባለስልጣናት ዘንድ ብስጭትን እንዳጫረ ተነግሯል::
=========/////////=========
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በጀመረው አዲስ የተቀናጀ ጦርነት ሚያዝያ 14/2016 ዓ/ም ከጎንደር ከተማ በቅርብ እርቀት ከጎንደር-ቆላድባ-አይንባ ባካለለ ሰፊ የጦር ግንባር ከባድ ተጋድሎ ሲያደርግ ውሏል።
በዚሁም የጦር ውሎ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ከበጌ ምድር ክፍለጦር ጋር ጥምረት ፈጥሮ ድል አስመዝግቧል::
በበጌምድር ክፍለጦር በኩል በሻለቃ አሌ የሚመራው ሻለቃ እና በራሱ በክፍለጦሩ መሪ አርበኛ ደረጀ በላይ የሚመራው ሐይል ተሳትፏል::
በጎንደሬ በጋሻው በኩል ደግሞ ጎንደር ከተማ በተደጋጋሚ እየገቡ ተልዕኮ የሚፈፅሙት ሁለት ሻለቃወች በሻንበል ሙሉሰው እና ወርቁ ዘገየ እየተመሩ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉ ውለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከከተማዋ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኑኙ ሲሆን ከተማውን ለህዝብ ደህንነት ሲሉ እንደለቀቁት ተናግረዋል።
በዚህ የተደናገጠዉ አገዛዙ ከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ የገባ ሲሆን ብዛት ያላቸዉን ወጣቶችን በጥርጣሬ እያሰረ መሆኑም ተገልጿል።
ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም ቆላ ወገራን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣቷ ይታወሳል።
==========////////=========
የአማራ ፋኖ በጎጃም በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አደረጉ።
ውይይቱ በጠቅላይ አዛዡ አርበኛ ዘመነ ካሴ እና በዋና ወታደራዊ አዛዡ በፋኖ ዝናቡ ልንገርህ መሪነት ተካሂዷዋል።
የአማራ ፋኖ ወደ አንድ ማዕከላዊ ኮማንድ መምጣት እና የዉስጥ ክፍተቶችን በመሙላት ጠንካራ አደረጀጃት መፍጠር የውይይቱ ዋና ሃሳቦች ናቸው ተብሏል::
በተጨማሪም በፋኖ ላይ የሚቃጡ የአሉባልታ ወሬዎችን እና በመንግስት ሚዲያ በኩል የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዋችን መምታት እና ማክሸፍ የሚቻልበትን አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዲሁም
ትግሉን በአጭር ጌዜ ለመቋጨት እየተደረጉ ባሉ ዝግጅቶች ሰፊ ውይይት ተደርጓል::