60 የአገዛዙ ወታደሮች በኤርትራ ጦር ታገቱ
በጎንደር በሁሉም አካባቢዎች ከፍተኛ ዉጊያ ሲደረግ ዋለ።
በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ፣መና መቀጠዋ፣ጉና በጌምድር እንዲሁም ጋይንት ወረዳ ጥጥራ ጎብጎብ፣እና ሳሊ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሲደረግ 105 የሚሊሻ እና የአድማ ብተና እጅ ሲሰጥ ከ50 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ድል ተደርጓል።
በኮለኔል ታደሰ የተመራዉ የጋይንት ጦር ከፍተኛ ድል ሲቀዳጅ ብዛት ያለዉ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣የቡድን እንዲሁም የትጥቅ እና ስንቅ አቅርቦት መማረኩን ለግዮን ቴሌሺዥን ገልጿል።
በዚሁ ቀጠና አንዳቤት ወረዳ የአንዳ ቤት ብርጌድ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እልህ አሰጨራሽ ዉጊያ በማድረግ በጠላት ሀይል ላይ ድል ተቀዳጅቷል።
አራት የአገዛዙን ተሽከርካሪ ከጥቅም ዉጭ የተደረገ ሲሆኑ ፣ከ30 በላይ የስራቱን ወታደር ድል ማድረግ ተችሏል። በዚህ አካባቢ በቅሎ ፍለጋ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ 3 ንፁሃን ዜጎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን የማህበረሰቡ ሀብትና ንብረት ሙሉ በሙሉ አዉድሞ መሸሹ ተገልጿል።
በዚህን ጉዳይ ላይ የጉና ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት መረጃዉን ሊያደርሰን በቀጥታ የስልክ መስመራችን ለይ ይገኛል
በተመሳሳይ በመና መቀዋ ከባድ ዉጊያ የተደረገ ሲሆን ብዛት ያለዉ የአድማ ብተና አባላት ምርኮ ተደርጓል።
አጊሳ ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የጠላት ጦር አካባቢዉን ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል።
በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ፣አይንባ፣ሰንበት ደብር እና ጎንደር ዙሪያ አራት ቀን የፈጀ ትንቅንቅ የተደረገ ሲሆን የአገዛዙን ሰራዊት የዉጊያ ታክቲክ በማበላሸት ፋኖ የበላይነቱን የወሰደ ሲሆን ተይዘዉ የነበሩ ቦታዋችን በማስለቀቅ በአገዛዙ ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረሱን የአፄዋቹ ሻለቃ አዛዥ ሻለቃ ሰለሞን አጠና ተናግሯል።
በሰሜን ጎንደር አጅሬ ጃኖራ፣ጃናሞራ፣ዳባት እና ደባርቅ ዙሪያ ከፍተኛ የተባለለት ዉጊያ የተደረገ ሲሆን የብልጽግና ዙፋን ጠባቂ ወታደር አፍሮ እና ተዋርዶ ተመልሷል።
በሻለቃ መሳፍንት ተስፋ ፣ሀብቴ ወልዴ ፣ሻለቃ ታደሰ፣ዶክተር አራጋዉ፣ባየ ቀናዉ እና በሌሎች የጦር ከዋከብት በጋራ የተመራዉ የጦር ዉሎ ለ18ኛ ጊዜ ሙከራ ያደረገዉን የአገዛዙን ሰራዊት ድል በማድረግ በመጣበት የሸኙት ሲሆን አብዛኛው የጠላት ሰራዊት ተበታትኖ በእየ አርሶ አደሩ ቤት መደበቁን የአይን እማኞች ለግዮን ቴሌቪዥን ገልፀዋል።
በምዕራብ ጎንደር የጎቤ መልኬ ክፍለጦር በሻለቃ ሲሳይ አሸብር እየተመራ ከታች አርማጭሆ እስከ ላይ አርማጭሆ ያለዉን ቀጠና በመቆጣጠር የአጠዛዙን ሰራዊት መዉጫ እና መግቢያ አሳጥተዉት ዉለዋል።
ከሁመራ የመጣውን የጠላትን ሀይል የደፈጣ ጥቃት በማድረስ ከፍተኛ ድል ያስመዘገቡ ሲሆን በትክል ድንጋይም ተመሳሳይ እርምጃ ተወስዷል።
በቋራ በሳሙኤል ባለድል የሚመራው የበረሃው ጦር ከመተማ እስከ አለፋ ያለዉን ቀጠና በመሸፈን እልህ አስጨራሽ አዉደዉጊያ የተደረገ ሲሆን ቋራን እና ሌሎች ቀጠናዋችንም በመቆጣጠር ከፍተኛ ጀብዱ መፈፀሙን የድል ጮራ ክፍለጦር አዛዥ ሳሙኤል ባለድል ለግዮን ቴሌቪዥን ገልጿል።
=======//////=======
ፋኖን የሚቀላቀሉ የአድማ ብተናና ሚሊሻ አባላት ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተነገረ።
በሰሜን ወሎ ዞን ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በቁጥር ከ40 በላይ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።
ተሀድሶ ተሰጥቷቸው ሰሜን ወሎ ዞን ተመድበው የነበሩ የአድማ ብተናና የፖሊስ አባላት መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ መቀላቀላቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ።
በተመሳሳይ
በዚህ ሳምንት ብቻ ከ400 በላይ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት በሁሉም የጎንደር አካባቢዎች ፋኖን ተቀላቅለዋል።
የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ፋኖን በብዛት እየተቀላቀሉ መሆኑንም የጎንደር ዕዝ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ተሾመ አበበው ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ተናግሯል።
በሚያዝያ 15 አዳር ብቻ 11 የአድማ ብተና አባላት፣ አንድ ብሬን፣ አንድ ስናይፐር እና ዘጠኝ ክላሽንኮቭ መሳርያ ይዘው የጸሃይቱን ክፍለጦር መቀላቀላቸውን ሻለቃ ተሾመ ለግዮን ቴሌቪዥን ገልጿል።
ሚሊሻ እንዲሁም አድማ ብተና ከፈረሰው ልዩ ሃይል መማር አለባቸዉ ያለው ሻለቃው መንግስት አሁንም ዳግም የቁማር ስራ ሊሰራ እየተዘጋጀ ስለሆነ ትጥቃቹህን ለጠላት አሳልፋቹህ ሳትሰጡ ፋኖን መቀላቀል አለባቹህ ሲልም መልእክቱን አስተላልፏል።
ወገኖቻችን በስቃይ ላይ መሆናቸዉን ተረድተንም ከስርአቱ በመውጣት የህልውና ትግሉን ማስቀጠል አለብን ሲልም ጨምሮ ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የአማራን መሬትም ሆነ ህይወቱን ለመንጠቅ ሰራዊቱን አዝምቶ በግፍ እየገደለ ባለበት በዚህ በዚህ ወቅት ከጠላት ጋር ተሰልፎ የሚዋጉ ወንድሞች ነቅተው ፋኖን መቀላቀል አለባቸዉ ብሏል::
========:////////=====
ሰሞኑን በደንቢያ በተደረገ ጦርነት ከ90 በላይ የጠላት ሀይል ድል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል ተባለ።
በዚህ አውደ ውጊያ ከ110 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳርያ ገቢ መደረጉንም የደንቢያ ፋኖ አዛዥ ሻለቃ ደረጀ በላይ ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ተናግሯል::
========:////////=====
ኤርትራ የአገዛዙን ሰራዊት ማገቷ ተገለፀ።
60 የሚደርሱ የአገዛዙ ወታደሮች በምስራቅ ትግራይ ዛላንበሳ በሚባል አካባቢ በፓትሮል በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በኤርትራ ጦር መታፈናቸዉን የአይን እማኞች ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ተናግረዋል።
የኢሳያስ አፈወርቂ ጦር የምስራቅ ትግራይን አብዛኛውን ቦታ ተቆጣጥሯል።
የኤርትራ ጦር አዲግራት ዘልቆ ለመግባት 25 ኪሎሜትር ብቻ የቀረዉ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ምንም ያሉት ነገር የለም።
በምስራቅ ትግራይ ሰፍሮ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊትም ሰሞኑን ከአካባቢዉ በመልቀቅ ወደ ሰሜን ጎንደር ማይፀብሪ እና ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ እንዲሰፍር መደረጉ ታውቋል።
የዛላንበሳ ከተማ ነዋሪዎች ለግዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን እደገለፁት ከምስራቅ ትግራይ የወጣው የአገዛዙ ሰራዊት ወታደሮች መንግስት ወልቃይትን ሊመልስላቹህ ስለሆነ ነው እኛ ወደ ወልቃይት የምንሄደዉ ብለውናል ሲሉም ገልፀዋል።
ወታደሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ እንኳን ደስ አላቹህ ወልቃይት ሊመለስላቹህ ነው በማለት ጭምር ለህዝቡ ሲናገሩ ነበርም ብለዋል።
በአሁኑ ሰአት የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ያልሆነውን ጦርነት በፀረ ሰላም ሀይሎች በኩል ህዝቡ ወደ ጦርነት እንዲገባ እየተደረገ ሲሆን በአላማጣ እና በአካባቢዉ ውጥረት እንዲነግስ እያደረገ ያለው የፌደራሉ መንግስት ነዉም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የፌደራሉ መንግስት ይህንን ያደረገዉ በአማራ ክልል የአስተዳደር ስርዓቱ በፋኖ ስለተነጠቀ እንደተለመደው ሁሉ ሁለቱን ህዝቦች አጋጭቶ ስልጣኑን ለማራዘም የሚያደረገው ሙከራ መሆኑንም ለግዮን ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
========:////////=====
ቀሲስ በላይ ቀን ቀን ታስሮ ማታ ማታ ወደ ቤቱ እንዲሄድ እንዲፈቀድለት የአገዛዙን ፍርድ ቤት ጠየቀ
ቀሲስ በላይ ለሁለተኛ ግዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል
የአገዛዙ ፖሊስ ቄሲስ በላይ የተደራጀ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ክስ አቅርቧል
ክሱ እንደሚያስረዳው ቄሲስ በላይ ወንጀሉን የፈፀመው ብቻውን ሳይሆን ሌሎችንም ግለሰቦች በማሳተፍ ጭምር ነው
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የግዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ተጠይቋል
እንዲናገር እድል የተሰጠው ቄሲስ በላይ ፍርድ ቤቱ ማታ ወደ ቤቱ እየሄደ ጠዋት ወደ እስር ቤት እንዲመለስ እንዲፈቅድለት ጠይቋል
ከዚህም በተጨማሪ አብረውት የታሰሩት የኦሮሞ ግብረ አበሮች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ቄሲስ በላይ ጠይቋል
ይህም ሁኔታ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለማነጋገር በቅቷል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት እስረኛ በሚፈልገው መንገድ እንዲታሰር የሚጠይቅባት ሀገር ተፈጥራለች
የግዮን ምንጮች ከአዲስ አበባ እንዳሉት ቄሲስ በላይ ቁልፍ የአገዛዙ ሰው ነው በህግ ሽፋን የታሰረውም ለይስሙላ ነው ባይ ናቸው በመሆኑም በቅርቡ እንደሚፈታ እነዚሁ ምንጮች አረጋግጠዋል።
========:////////=====
በአዲስ አበባ አመፅ ሊቀሰቀስ እንደሚችል የካናዳ መንግስት አስጠነቀቀ
ካናዳውያን በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ከመሄድ እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል
የኢትዮጵያ ጉዳይ ከቀን ወደ ቀን እያሳሰባቸው ካሉ የምእራብያውን ሀገራት ውስጥ ካናዳ አንዷ ነች
የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ብሏል
በመሆኑም ካናዳውያን በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ ከመሄድ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ በስተቀር ሰላም የለም ያለው መግለጫው በአዲስ አበባም ቢሆን በቅርቡ አመፅ ሊቀሰቀስ ይችላል ብሏል
በአዲስ አበባ የሚነሳውም አመፅ ጉልበትና ግድያን መነሻ ያደረገ ሊሆን እንደሚችል የካናዳ መንግስት ስጋቱን አጋርቷል
በመሆኑም አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ዜጎች ሁኔታውን በንቃት እንዲጠብቁ አሳስቧል በከተማዋ እየጨመሩ የመጡ ከባባድ ወንጀሎችም አሳሳቢ ነው በማለት የካናዳ መንግስት ገልጿል በመሆኑም የካናዳ ዜጎች ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቋል
የካናዳ መንግስት አገዛዙ ሁኔታዎች ከቁጥጥሩ ውጭ እየወጣበት ስለመሆኑ ሲገልጽ የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም እንግሊዝ አሜሪካና ሌሎችም የምእራቡ አለም ሀገራት ኢትዮጵያ ውስጥ ከባድ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል ማስጠንቀቅ ከጀመሩ ውሎ አድሯል
አገዛዙ በተደጋጋሚ ሀገሪቱ ሰላም ነች ሁሉም ነገር በቁጥጥሬ ስር ነው በማለት ቢለፍፍም ከግማሽ በላይ የሀገሪቱ አካባቢዎች የት እንዳሉ እንኳን አያውቁም
ይህንን በተደጋጋሚ የሚገመግሙት ምእራባውያን ሀገሪቱ ላይ ታይቶ የማይታወቅ የመበታተን አደጋ ሊከሰት ይችላል እያሉ ነው
የአገዘ ቁንጮ ግን እንኳን የምድሩን በሰማይም ነገት አስገባችኋለሁ እያለ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መሳለቁን ቀጥሏል።