ባህር ዳር የአገዛዙ ራዳር መቆጣጠሪያ በፋኖ ተያዘ
ፋኖ በባህርዳር ዙሪያ ያለውን የአገዛዙን ራዳር መቆጣጠሪያ ጣቢያን መቆጣጠሩን ቃል አቀባዩ ማርሸት ፀሀዩ ገለፀ
ቃል አቀባዩ እንዳለው የራዳር መቆጣጠሪያውን ለመያዝ የተወሰነ ውጊያ ተደርጓል በአካባቢው የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮችም ተማርከዋል ፋኖ ማርሸት እንዳለው የተወሰደው እርምጃ አገዛዙ እንኳን ህዝቡ ራሱንም ማዳን እንደማይችል ያረጋገጠ ነው
በዚህም መሠረት አገዛዙ በአሁኑ ወቅት በሰሜን በኩል የሚደረገውን የአውሮፕላን እንቅስቃሴ መቆጣጠር አይችልም
ድሮንም እንዳይጠቀም አድርገነዋል ሲል ቃል አቀባዩ ገልጿል::
==========//////////========
ፋኖ ባህርዳር በሚገኙ ካድሬዎች ላይ እርምጃ ወሰደ:: እርምጃው የተውደው ካድሬዎቹ ህዝቡን በግድ ግብር ለማስከፈል በመሞከራቸው ነው::
በዚህም ምክንያት ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል
ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም የአገዛዙ ግብር ሰብሳቢ ሱቅ ለማሸግ ሞክሮ ነበር ሆኖም መረጃው የነበራቸው ፋኖዎች ተኩስ በመክፈት የአገዛዙን ቡድን በትነውታል
ፋኖ የአገዛዙ ካድሬዎች ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፅሙ በምክር እና በአነስተኛ እርምጃዎች ሲያስተምር ቆይቷል ሆኖም ከዚህ በማይማሩት ላይ እርሞጃ እየተወሰደ ነው ተብሏል
ዛሬ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የአገዛዙ ወታደሮች በአንዲት ሰላማዊ ሴት ላይ መጠነኛ ጉዳት ከማድረሳቸው በቀር ጉዳት አልደረሰም
ሰምኑን የአማራ ፋኖ በጎጃም ደጉ በላይ ሻለቃ ባህርዳር ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በተከታታይ ጥቃት በማድረስ በአገዛዙ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል ።
በዛሬው ዕለትም የአማራ ፋኖ በጎጃም ደጉ በላይ ሻለቃ በዘንዘልማ ቀጠና አንድ የገቢዎች መኪና እና አንድ ፒካፕን በቦምብ አጋይተዋል በዚህም ጥቃት የአገዛዙ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ተገድለዋል
በዚህ የተበሳጨው አገዛዙ የፋኖ ቤተሰቦችን እያፈነ መውሰዱን ቀጥሏል ። በዛሬው እለት ብቻ በርካታ የታጋይ እናቶችን አፍኖ እንደወሰደ ከቦታው የተገኙ መረጃዎች አረጋግጠዋል::
==========//////////========
በብልፅግናዉ አገዛዝ እውቅና ተሰቷቸው ህዝብን ሲዘርፉ የነበሩ ዘራፊዋች በፋኖ እርምጃ ተወሰደባቸዉ!!
ከደብረታቦር ጋይንት ወሎ በሚያገናኛዉ አዉራ ጎዳና ላይ ተሰማርተው በአገዛዙ ሰራዊት ጭምር አገዛ እየተደረገላቸው ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር አቅራቢያ ልዩ ስሙ አለም ሳጋ ተብሎ በሚጠራዉ ጫካ ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር በመሆን ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩ ባንዳዎች እርምጃ ተወስዷባቸዉል።
በተመሳሳይ ከደብረታበር ጋይንት በሚወስደዉ አዉራ ጎዳና ልዩ ስሙ ጋሳይ፣ጉና በጌምድር ወረዳ ጥጥራ፣ጋይንት ወረዳ ጎብጎብ እና ሳሊ መቀመጫቸውን አድርገዉ ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩና ዘራፊች ሙሉ ለሙሉ መደምሰሳቸዉን የጎንደር ዕዝ የጦር አዛዥ ኮሎኔል ታደሰ ለግዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን ገልጸዋል::
=========//////////========
ጎንደር አጅሬ ጃኖራ፣አንቃሽ አንዲሁም አርባያ በለሳ ከአገዛዙ ነፃ መዉጣታቸዉ ተገለፀ።
በአሁኑ ወቅት የጎንደር ፋኖ አብዛኛውን የጎንደር አካባቢ ተቆጣጥሯል
በርካታ ድሎችም እንደተመዘገቡም የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ለግዮን ሳተላይት ቴሌቭዥን ገልፀዋል።
በሌላ በኩሎ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አርባያ እና በለሳን ተቆጣጥሮ አድሯል።
ዛሬ ለሊት ላይ በተሰራ ተልዕኮ የጠላትን ሐይል ድባቅ በመምታት አርባያ ከተማን ተቆጣጥሮ አድሯል። ተልዕኮውን የወሰደው በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ኮማንዶ ያለው አዱኛ የሚመራው መብረቅ ብርጌድ ነው ተልእኮው እጅግ መናበብ የተሞላበትና ውጤታማ እንደነበር ሻለቃ ቆማንዶ ያለው ገልጸዋል::
ተልእኮው የብልፅግና አመራሮችን ኢላማ ያደረገ እና በቦንብ የታጀበ ድንገታዊ ጥቃት የታየበት ነው ተብሏል
በአሁኑ ሰዓት የብልፅግና መከላከያ ሐይል ከደጎማ ወደ አርባያ እየመጣ ሲሆን ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል ከከተማ ወጣ ብለን በቅርብ እርቀት ላይ እንገኛለን ሲል ሻለቃው ጨምሮ ተናግሯል። ምዕራብ በለሳ ሙሉ በሙሉ በእኛ ቁጥጥር ነው ያለው ቃል አቀባዩ የብልፅግና ገዳይ ቡድን ከአስፖልት ማለፍ የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብሏል።
=======////////=======
አገዛዙ በሰው ልጆች ላይ የሚደረጉ ወንጀሎችን በሙሉ እንደፈፀመ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ የአገዛዙ ባለስልጣናት የጦር ወንጀል ፈፅመዋል ከዛም ሲያልፍ ዘረፋ ላይ ጭምር በስፋት መሳተፋቸውን አስታውቋል
መግለጫውም ጨምሮ እንዳለው አገዛዙ ጋዜጠኞችን ያዋክባል ያስራል ከዚህም በተጨማሪ የሲቪክ ማህበራትንም እንደሚያዋክብ ጭምር ገልጿል ይህም ተቀባይነት እንደሌለው አሳስቧል
አገዛዙ የህግ የበላይነትን ለማክበር ፍላጎት የለውም ያለው መግለጫው ትንንሽ ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሞክር ግን ገልጿል
አገዛዙ በተለይ በአማራ ክልል ንፁሐንን መግደሉ እንደተረጋገጠ የገለፀው የአሜሪካ ሪፖርት ይህም ተመዝግቦ ተቀምጧል በማለት አስጠንቅቋል
ከአገዛዙ በተጨማሪም ህወሀትን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች በሰው ልጆች ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ብሏል
በዚህ የተደናገጠው አገዛዙ ዛሬ በልሳኖቹ ባወጣው ረዥም መግለጫ ሀገሪቱ የተረጋጋች ነች ሲል አትቷል
መግለጫው ኦነግ ሸኔን አንዳንድ ቦታዎች ብቻ የተቆጣጠረ በማለት ሲገልፀው ፋኖን በተመለከተ ግን ቀሪ ስራዎች አሉብኝ በማለት አምኗል::
አሜሪካ ከአገዛዙ ሰዎች ጋር ከተቆራረጠች ውሎ ያደረ ሲሆን አሁን ወደ ቅጣት ምእራፍ የተሸጋገረች ይመስላል::
==========////////========
የብልፅግና ተደራዳሪዎች ፋኖን በጋራ እንውጋ ሲሉ ሀሳብ አቅርበውልን ነበር ሲል የኦነግ ሰራዊት አጋለጠ
ብልጽግና ታጣቂዎችን ትጥቅ ከማስፈታት ውጭም ምንም ፍላጎት የለውም ሲል የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት ገልጿል
ሰራዊቱ አብይ አህመድ ትላንት ላወጣው ሰፊ መግለጫ ምላሽ ሰቷል ኦነግ እንዳለው አገዛዙ ህዝብንና አለም አቀፉን ማህበረሰብ በማደናገር ቀጥሏል
ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ ለማግኘት የማባበያ ሀሳቦችን እየደረደረ ይገኛልም ብሏል
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑም የአገዛዙን እድሜ ከማራዘም በላይ ዋጋ እንደሌለው ኦነግ አስታውል አገዛዙ ለሰላም ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ ታንዛኒያ የተደረገው ድርድር ይሳካ እንደነበር የእነግ ሰራዊት መሪው ጃል መሮ ጨምሮ ገልጿል
ጃልመሮ እንዳለው በታንዛኒያ ስብሰባው ወቅት የአገዛዙ ሰዎች እንታረቅና ፋኖን እንውጋ ሲሉ ነበር
በዚህም ብቻ ሳያበቁ ኤርትራ ሄደን ወደብ እናምጣ ሲሉም እንደነበር ጃልመሮ አጋልጧል በመሆኑም የኦነግ ሰራዊት አገዛዙ ለሰላም ፍላጎት አለው ብሎ እንደማያምን ተመልክቷል::