ፋኖ የአገዛዙን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጥሪ አልቀበልም አለ
ፋኖ የአገዛዙን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጥሪ ውድቅ አደረገ::
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በኦሮሙማ ካድሬዎች እየተዘረፈ እንደሚገኝ የግዮን ምንጮች አረጋግጠዋል።
አገዛዙ ሲጨንቀው ካቋቋማቸው ወኪሎቹ ውስጥ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አንዱ ነው።
በአገዛዙ ቁንጮ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚሰጠው ይህ ኮሚሽን የህዝብን ሀብት ከመዝረፍ በላይ ለብልፅግና ፖለቲካዊ ስራዎችን በመስራት ተግባራት ላይ ተጠምዷል።
ኮሚሽኑ በቅርቡ የአማራ ፋኖ ወደ ሰላም ድርድር እንዲመጣ ጥያቄ ማቅረቡ አይዘነጋም ኮሚሽኑ እንደሚለው ፋኖ ወደ ድርድር ከመጣ በአለም አቀፍ ህግ መሠረት ሙሉ ዋስትና ይሰጠዋል ለዚህም ሀላፊነቱን ኮሚሽኑ እንደሚወስድ አረጋግጧል።
ሆኖም ፋኖ በሰጠው ምላሽ ኮሚሽኑ መሠል አሰተያየቶችን ከመስጠት እንዲታቀብ አስጠንቅቋል ኮሚሽኑ የአማራ ህዝብን የጅምላ ግድያ እያበረታታ ነው ያለው ፋኖ ጥያቄውን እንደማይቀበል አረጋግጧል።
አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማደንዘዝ ከመሰረታቸው ተቋሞች ውስጥ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አንዱ ነው በእርግጥ የኮሚሽኑ አመራሮች ሰላም ይመጣል የሚል ተስፋ አላቸው ይባላል ያላቸውም የኋላ ታሪክ በኢትዮጵያዊነት ባህል ያደጉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
ሆኖም ሰው በላ እና ነውረኛ የሆኑት የኦህዴድ ካድሬዎች ኮሚሽኑ ውስጥ በመሰግሰግ ፖለቲካዊ ስራ ከጀመሩ ውለው አድረዋል።ኦሮሙማዎቹ ከዚህም አልፈው የኮሚሽኑን ሀብት እየዘረፉ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ የግዮን ቴሌቪዥን ምንጮች በማስረጃ አረጋግጠዋል የኮሚሽኑን ፍላጎት በመተውም ጣልቃ በመግባት ቤቱን የኦሮሞ መናሀሪያ ካደረጉት ሰንብተዋል።
በዚህ ደረጃ በኦሮሙማ ካድሬዎች የተጨመላለቀው የምክክር ኮሚሽኑ ለፋኖ እንነጋገር ብሎ መጠየቁ በብዙዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ጥሎታል ተብሏል ይህም ቢሆን ግን ፋኖም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ሰራዊትም ኮሚሽኑን ራስህን ቻል ብለውታል።
===========///////=============
አገዛዙ በሽብር ወንጀል ከስሻቸዋለሁ ያላቸውን አማራውያንን ፍርድ ቤት አቀረበ።
በጋዜጠኛ መስከረም አበራ ላይ ማስረጃ ያጣው የኦሮሙማው ቡድን ጭንቀት ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል።
የአማራ ነፃነት ታጋዮቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ምንም ጥፋት እንደሌለባቸው አስረድተዋል።
የአገዛዙ ፍርድቤትም ለአቃቢ ህግ ምስክር እንዲያሰማ ቢጠይቅም አቃቢ ህግ ተብዬው ምስክሮች መቅረብ እንደማይችሉ ተናግሯል።
ለዚህም ምክንያት ያለው ምስክሮች ከታወቁ በቀል ሊደርስባቸው ይችላል የሚል ነው።
በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ፍርድ ቤት ለግንቦት 12 ውሳኔ ለመስጠት ቀጥሯል።
ግዮን ቴለቪዥን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተቋሙ ምንም ማስረጃ የለውም።
በተለይ በመስከረም አበራ ላይ የሚቀርብ ማስረጃ በመጥፋቱ ጭንቀቱ በርትቷል።
ይህም ቢሆን ግን ጋዜጠኛዋን እስር ቤት እያሸ እስከቻለው ድረስ ሊበቀላት እንዳሰበ የፍትህ ሚኒስቴር ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
መስከረም አበራ በተደጋጋሚ የታሰረችው ወንጀል ሰርታ ሳይሆን ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሙማ ሰዎች ላይ ምህረት የለሽ ትችት በማቅረቧ እንደሆነ አለም ከተረዳው ውሎ አድሯል።
አዲስ አበባ ውስጥ አስተያየት የሚሰጡ የአገዛ ካድሬዎች ለእኛ ንቀት አለባት የሚል ቅሬታ በመስከረም አበራ ላይ ሲሰጡ መስማት የተለመደ ሆኗል ይህም ቢሆን ግን መስከረም አበራ የአገዛዙ ፊልድ ማርሻል ማእረግ ከመሸከም ባሻገር ምንም እውቀት እንደሌለው በአደባባይ በመናገር ብርሀኑ ጁላን ስትጫወትበት መሰንበቷ አይዘነጋም።
===========///////========
ከሃያ አምስት በላይ የአድማ ብትና አባላት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ አሳምነው ጽጌ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: የአድማ ብተና አባላቱ በአማራ ህዝብ ላይ ጥፋት እንጅ ክህደት አልፈጸምንም ብለዋል::
የብልጽግና አገዝዙ የአማራን ህዝብ ዳግም ለባርነት አሳልፎ ሊሰጥ እንደሆነ የተረዱትን ዘግይተው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ከፋኖ ጋር በመቀላቀላቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል::
ወደፊትም የትኛውንም ግዳጅ ከአማራ ህዝብ ጎን ሆነው ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል::
በተጨማሪም የደቡብ እና የሰሜን ወሎ ዞኖችን አጠቃሎ የያዘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ የአንድነት ጉዳይ ላይ በትኩረት እየሰሩና በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝኙም ገልጸዋል::
==========/////////==========
የምስራቅ አማራ ፋኖ ከህዝብ ጋር ውይይት አደረጉ:: በውይይቱ በዋናነት ብልፅግና የአማራን ህዝብ ለመከፋፈል ትኩረት አርጎ እየሰራ ይህንንም ተንኮል ቀድሞ መረዳት እንደሚገባ ተገልጿል::
ለረጅም አመታት መከላከያ ስራዊት አባላት የነበሩ በአሁኑ ወቅት መከላከያን ከድተው ፋኖን የተቀላቀሉ ታጋዬች ንግግር አድርገዋል:: የአገዛዙን በርካታ ሚስጥሮችም አውጥተው ተናግረዋል::
የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ እርስ በርስ ለማጨራረስ የሚያደርገውን ሴራ ቀድሞ ማክሸፍ እንደሚገባ ተገለፀ::
የምስራቅ አማራ ፋኖ ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይት አገዛዙ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አዳዲስ አጀንዳዎችን በመፍጠር ተጠምዷል::
በቅርቡ በባህር ዳር 5 ሙስሊሞችን በራሱ ሰራዊቶች በማስገደል የሃይማኖት ጦርነት ለመቀስቀስ ያደረገው ሙከራም ሳይሳካለት ቀርቷል::
የምስራቅ አማራ ፋኖ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይትም የተገደልነው በሃይማኖት ሳይሆን በዘራችን ተመርጠን ነው ሲሉ ተደምጠዋል:: በተለይም ለወሎ ህዝብ ስለሃይማኖት እኩልነት ማስተማር ሞኝነት ነው በማለት ተናግረዋል::
ብልፅግና እየሄደበት ያለው የጠብ አጫሪነት አካሄድ የአማራን ህዝብ ስነልቦና አለመረዳቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል::
የአማራን ህዝብ በመግደልና በማሳደድ የተጠመደው ብልፅግና ብዙ ሙከራዎች አለመሳካታቸው ብስጭት ውስጥ ከቶታልም ነው የተባለው::
በቅርቡ የመጨረሻ ሙከራውን ለማድረግ የፕሪቶሪያ ስምምነቱን በመጣስ በርካታ የአማራ ግዛቶች በህውሃት እንዲወረሩ እንዳደረግም የሚታወቅ ነው:: በዚህም ከ50 ሺህ በላይ አማራዎች ተፈናቅለዋል::