በሕወሐት ወረራ 50 ሺ ተፈናቃዮች እንዳሉ ኦቻ አስታወቀ።
ከግዮን ሳተላይት ቴሌቪዥን የሚያዝያ 24/2016 ዓም ዜና ይዘን ቀርበናል:፡ ሙሉቀን ገበያው ነኝ። በቅድሚያም አበይት ርእሶቹን።
========////////=====
የአፍሪካ ኅብረት በሕገ ወጥ መንገድ ከንግድ ባንክ አካውንቱ ሊወጣ የነበረው ስድስት ሚሊዮን ዶላር መክሸፉን አስታወቀ።
አገዛዙ የማህበረ ቅዱሳን ሊቀመንበር ዋና ፀሀፊን እና ሌሎች የሃይማኖት አባቶችን አፍኖ ወሰደ።
በቆቦ አካባቢ ያሉ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደየቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ።
========:////////=====
ዝርዝር ዜና።
—————
የአፍሪካ ኅብረት በሕገ ወጥ መንገድ ከንግድ ባንክ አካውንቱ ሊወጣ የነበረው ስድስት ሚሊዮን ዶላር መክሸፉን አስታወቀ።
የአፍሪካ ኅብረት ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስድስት ሚሊዮን ዶላር በሕገ ወጥ መንገድ ለማውጣት የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱን ገልጿል።
የአፍሪካ ኅብረት “ሊደርስበት ይችል የነበረውን ኪሳራ መቀልበስ ተችሏልም ብሏል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ለመመሥረት እንቅስቃሴ በማድረግ እና ከአገዛዙ ጋር በጥምረት በመስራት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።
የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫም ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ. ም. “የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኛ ባልሆነ አካል የክፍያ ትዕዛዝ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ” ገብቷል።
“ከግንባታና የውሃ ቁፋሮ ሥራ” ጋር ለተያያዘ ክፍያ በሚል ገንዘቡ ሊወጣ እንደነበርም የኅብረቱ መግለጫ ያስረዳል።
ሆኖም ግን በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የፋይናንስ ዳይሬክተር በተደረገ “ጥልቅ ምርመራ” ክፍያውን ለማውጣት የገባው ሰነድ ሐሰተኛ መሆኑ እንደተደረሰበትም ተገልጿል።
የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን “ከፍተኛ ሥፍራ ሰጥቶ” እየተከታተለው እንደሆነ እና “እንዲህ ያለ ሙከራ መደረጉም አሳሳቢ ቢሆንም ክስተቱ በኅብረቱ ያለውን “የደኅንነት ጥንቃቄ መልሶ ለማጤን” ምክንያት እንደሆነ ጠቅሷል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
========////=========
በተያያዘ ዜና በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠረው ቀሲስ በላይ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት በአገዛዙ ፍርድ ቤት መፈቀዱ ታውቋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ሐሙስ 24/ 2016 ዓ. ም. ረፋድ ላይ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎው ነው።
ቀሲስ በላይ እንዲሁም አብረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት አጃቢው እና ሹፌሩ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
“በሐሰተኛ ሰነድ በመገልገል፣ የሙስና ወንጅል በመፈጸም እና በከባድ አታላይነት” ክስ በቀረበበት ቀሲስ በላይ ላይ ከዋስትና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ ክርክር ውስጥ ገብቷልም ተብሏል።
በስተመጨረሻም 15 ክስ የመመስረቻ ቀናት በፍርድ ቤቱ ተሰጥቷል።
========////========
አገዛዙ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ አዲስ ዘመቻ ጀምሯል።
አሁን ላይም የማህበረ ቅዱሳን ሊቀመንበር ዋና ፀሀፊን ማሰሩ ታውቋል።
አገዛዙ ጦርነት ከከፈተባቸው ሀይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዷ ናት።
ቤተክርስቲያኗን ለመበታተን ከአንድ አመት በፊት ቢሞክርም ምእመኑ ፅኑ ሆኖ በመቆየቱ ቤተክርስቲያኗ ተርፋለች።
ይህም ቢሆን ግን ከቤተክርስቲያን ላይ እጁን ለአፍታ ማንሳት የማይፈልገው የአገዛዙ ቁንጮ አዳዲስ እቅዶችን ይዞ መጥቷል።
ከእቅዶቹ መካክልም በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን በኩል የዘረፋ ተግባር ላይ መሠማራት ነው
የመጀመሪያ ምርጫቸውም የአፍሪካ ህብረትን መመዝበር ቢሆንም ዘረፋው ሳይሳካ ቀርቶ ቄሱም እስር ቤት ገብቷል።
በሁኔታው ጥብቅ ውሳኔ እንደሚወስን ያስታወቀው የአፍሪካ ህብረትም ጉዳዩ ትኩረት ካልተሰጠው አካውንቴን ወደ ሌላ ሀገር እወስዳለሁ ብሎ ዝቷል።
የአሜሪካ ድምፅ እንደዘገበው ህብረቱ የታቀደ ዝርፊያ ለመፈፀም ተሞክሮብኛል የሚል እምነት አለው።
በሁኔታው የተደናገጠው አገዛዙ በቄሱ ላይ ክስ እንዲመሰረት አዟል።
ጉዳዩም በቄሱ ላይ ብቻ ተደፍድፎ እንዲዘጋ አገዛዙ እየተሯሯጠ መሆኑን የግዮን ቴቪ ምንጮች አረጋግጠዋል።
አገዛዙ ጉዳዩን ለዘብ ለማድረግና ትኩረት ለመቀየርም አሁን ላይ ሌላ ሴራ ጀምሯል።
እሱም የማህበረ ቅዱሳን ሊቀመንበርና ዋና ፀሀፊውን ከመኖሪያ ቤታቸው አፍኖ በመውሰድ ለእስር ዳርጓል።
የቄስ በላይን ቅሌት ለግዜው ጋብ ያደርግልኛል ብሎ ያሰበው አገዛዙ ከድራማ የዘለለ እውቀት እንደሌለውም የግዮን ምንጮች ተናግረዋል።
========:////////=====
በተመሳሳይ ዜና አገዛዙ ሚያዝያ 23 ሌሊት መምህር ኃይለሥላሴ ጽጌን
አፍኖ መውሰዱ ታውቋል።
መምህር ሃይለስላሴ ጽጌ ሰላም የብ/ጀነራል አሳምነዉ ጽጌ ታናሽ ወንድም ናቸው።
በአገዛዙ አፋኝ ቡድን ሚያዝያ 23 2016 ኣም ታፍነው መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በተያያዘም በደቡብ ምእራብ አፍሪካ ሀገራት ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሊቀማእምራን ብርሀኑ ተክለያሬድ በአገዛዙ ወታደሮች መታሰራቸው ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ምንጮቻችን እንደሚሉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታዊ መሪዎች ላይ እስሩ ሊቀጥል ይችላል።
በአሁኑ ሰአትም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል ተብሏል።
========:////////=====
በቆቦ አካባቢ ያሉ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደየ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ
ቢሆንም ግን አሁንም በርካታ ተፈናቃዮች በአካባቢው ይገኛሉ።
በዚህም መሠረት በቆቦ ወደ 17 ሺህ ተፈናቆዮች ሲገኙ ሰቆጣ አካባቢ ደግሞ ወደ ስምንት ሺህ ገደማ ተፈናቃዮች እንዳሉም ኦቻ አስታውቋል።
ለተፈናቀሉት ሰዎች የሚደረገው የድጋፍ መጠን በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቋል።
በአካባቢው ያሉ የአገዛዙ ባለስልጣናት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡም አስጠንቅቋል።
በአካባቢው በነበረው ችግር 149 ትምህርት ቤቶች መዘጋጀታቸውን አንዳረጋገጠም ገልጿል።
አካባቢው ላይ ያለው የጠላትነት መንፈስ ለአደጋው ምክንያት ነው ያለው ኦቻ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለችግሩ በቂ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስቧል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ህወሀት በፈፀመው ወረራ 50 ሺ ያህል ሰዎች መፈናቀላቸው አይዘነጋም።
ሆኖም በተሰራው ስራ የተወሰኑት ወደ ቤታቸው ቢመለሱም አደጋው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው።
========:////////=====